የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና የሀገር ሽማግሌዎች በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና ትግራይ ክልል መንግስት መካከል ያለው መልካም ያልሆነ ግንኙነት በንግግር እንዲፈታ ጥረት ለማድረግ ዛሬ መቐለ ገቡ፡፡ የኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖት ተቋማት መሪዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ያካተተው ይህ ቡድን ዛሬ ጠዋት መቐለ ደርሶ አሁን ላይ ከትግራይ ክልል መንግስትና ህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በዝግ እየመከረ ነው፡፡ ከሽማግሌዎቹና የትግራይ ክልል መንግስት አመራሮች ውይይት በኋላ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡