1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ መፅሐፍ በሀረርጌ ኦሮሞ ታሪክ ፣ ባህል እና እሴት ላይ

ዓርብ፣ ኅዳር 13 2017

በሀረርጌ ኦሮሞ ታሪክ ፣ ባህል እና እሴት ላይ በማተኮር የተዘጋጀው መፅሐፍ በሀረር ለምረቃ በቅቷል። በኦሮሚያ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲቲዩት በምስራቅ ሀረርጌ አካባቢ በሚኖሩ የሀረርጌ ኦሮሞዎች ታሪክ ላይ የተዘጋጀው መፅሀፍ ማህበረሰቡ ታሪኩን እንዲያውቅ ከማድረግ ባለፈ ትክክለኛውን ታሪክ ለመሰነድ ያስችላል ተብሏል ።

https://p.dw.com/p/4nK7W
Äthiopien Studie des Oromo-Forschungszentrums
ምስል Messay Teklu/DW

አዲስ መፅሀፍ በሀረርጌ ኦሮሞ ታሪክ ፣ ባህል እና እሴት ላይ

በሀረርጌ ኦሮሞ ታሪክ ፣ ባህል እና እሴት ላይ በማተኮር የተዘጋጀው መፅሐፍ በሀረር ለምረቃ በቅቷል። በኦሮሚያ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲቲዩት በምስራቅ ሀረርጌ አካባቢ በሚኖሩ የሀረርጌ ኦሮሞዎች ታሪክ ላይ የተዘጋጀው መፅሐፍ ማህበረሰቡ ታሪኩን እንዲያውቅ ከማድረግ ባለፈ ትክክለኛውን ታሪክ ለመሰነድ ያስችላል ተብሏል ።

በኦሮሚያ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲቲዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ አስራት መፅሐፉ በምስራቅ ሀረርጌ አካባቢ በሚኖሩ የሀረርጌ ኦሮሞዎች ሁለንተናዊ ታሪክ የተካተተበት መሆኑን ገልፀዋል።
በሀገሪቱ ትክክለኛ ታሪክ እና ትርክት አለመኖር ምን ያህል ዋጋ እያስከፈለ እንደሆን ያነሱት አቶ ዝናቡ ስራችን ያንን ማስተካከል ነው ብለዋል።

መፅሐፉ ለትውልዱ ትልቅ ፋይዳ አለው ያሉት ደግሞ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱረህማን ናቸው።
የሀረርጌ ተወላጅ የሆኑት አቶ መሀመድ አህመድ ቆፔ የታሪክ መፃፉ ጅምር በየአካባቢው ያለውን ህዝብ ታሪክ በመፃፍ የኢትዮጵያ ህዝቦች የጋራ ታሪክ የሚፃፍበትን አቅጣጫ ለማመላከት እንደሚረዳ ተናግረዋል።
በሀረር በተካሄደው የመፅሀፍ ምረቃ ባለስልጣናት ፣ አባገዳዎች የተለያዩ እንግዶች ተገኝተዋል።

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

መሳይ ተክሉ
ታምራት ዲንሳ
ፀሀይ ጫኔ