1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢው የአንበጣ ወረራ በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ጥቅምት 8 2013

ኢትዮጵያ ላይ የተከሰተው መጠኑ የበዛው የአንበጣ መንጋ ካለፉት ሳምንታት ወዲህ የብዙዎች ትኩረት ስቧል። ላለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም ከ2011 ጀምሮ የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት መጠኑ የበዛ የአንበጣ መንጋ ለምሥራቅ አፍሪቃ እንደሚያሰጋ ሲያሳስብ ነው የሰነበተው።

https://p.dw.com/p/3k3IX
Äthiopien | Heuschreckenplage an der Grenze zu Tigray und Amhara
ምስል Million H. Silase/DW

እንወያይ፦ አሳሳቢው የአንበጣ ወረራ በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ላይ የተከሰተው መጠኑ የበዛው የአንበጣ መንጋ ካለፉት ሳምንታት ወዲህ የብዙዎች ትኩረት ስቧል። የአንበጣው መንጋ እንዲህ በብዛት ተከስቶ ሲታይ ከ25 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገልጿል። ላለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም ከ2011 ጀምሮ የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት መጠኑ የበዛ የአንበጣ መንጋ ለምሥራቅ አፍሪቃ እንደሚያሰጋ ሲያሳስብ ነው የሰነበተው። የግብርና ሚኒስቴር መረጃውን አግኝቻለሁ፤ በምችለው አቅምም ዝግጅት አድርጌያለሁ ቢልም በአምስት ክልሎች እና በአንድ የከተማ አስተዳደር የአንበጣው መንጋ የተጠናከረ ወረራውን አድርጎ የደረሰ ሰብል እያወደመ ነው። አዝመራው ሰምሯል እየተባለ የአንበጣው መንጋ እያደረሰ ያለው ጉዳት ወደጎተራ የሚያደርሰው አይመስልም። በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ መንገድ የሚደረገው የመከላከል ርብርብ አንበጣ የሚያደርሰውን ጉዳት ማስቀረት ባይቻል መቀነሱ ይሳካለት ይሆን? ሙሉ ውይይቱን ከድምፅ ማዕቀፉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ