1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል

እሑድ፣ የካቲት 17 2016

ኢሰመኮ በቅርቡ በመርዓዊ ከተማ በሲቭሎች ላይ በመከላከያ ሠራዊት ከሕግ ውጭ ግድያዎች መፈጸሙን ለማወቅ መቻሉን አስታውቋል። በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር ያረጋገጠው መንግሥት የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዓይነት ሲቪል ዒላማ አላደረገም ሲል አስተባብሏል።

https://p.dw.com/p/4cp2x
Ethiopian Human Rights Commission about SNNPR human rights case
ምስል Ethiopian Human Rights Commission

አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል

ባለፈው ዓመት በነሐሴ ወር በአማራ ክልል የተጀመረው ጦርነት አሁንም መፍትሄ ሳያገኝ እንደቀጠለ ነው። በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ውጊያ ከሕግ ውጭ በሲቭሎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች አሳሳቢ ሆነው ቀጥለዋል ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በሚያወጧቸው መግለጫዎች እያሳወቁ ነው።

ከመካከላቸው ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን  በቅርቡ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በመርዓዊ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት በሲቭሎች ላይ ተፈጽመዋል ስለተባሉ ከሕግ ውጭ የተካሄዱ ግድያዎች ይፋ ያደረጋቸው መረጃዎች ይጠቀሳሉ። በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር ያረጋገጠው መንግሥት የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዓይነት ሲቪል ዒላማ አላደረገም ሲል አስተባብሏል።

ስለ መርዓዊ ከተማ ግድያ የዓይን እማኝ ምስክርነት

ያም ሆኖ ከመርዓዊው ግድያ በኋላ በሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ዜጎች የጥቃት ዒላማ መሆናቸው መቀጠሉ እየተዘገበ ነው።እንወያይ፤ በአማራ ክልል የቀጠለዉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማቆምያዉ የት ነዉ?

በአማራ ክልል የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አንድምታው

«አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል »መከላከያውና ዘላቂ የመወያያ ርዕሳችን ነው ። በዚህ ርዕስ ላይ  አቶ ባይሳ ዋቅወያ  የዓለም አቀፍ ሕግ ምሁርና በተለያዩ ሀገራት የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን ሆነው ያገለገሉ፣ ዶክተር ሺፈራው ገሰሰ መቀመጫውን አሜሪካን ያደረገው ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት ሊቀመንበር ፣ አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ፣አቶ አምሀ መኮንን የሕግ ባለሞያዎች ለሰብዓዊ መብቶች የተባለው ድርጅት ዋና መስራችና ስራ አስኪያጅ ተወያይተዋል።

ሙሉውን ውይይት ለማድመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ

ኂሩት መለሰ