1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አርበኞች ግንቦት ሰባት በመጪው ምርጫ በ547 ወረዳዎች ለመወዳደር ማቀዱን አስታወቀ 

ማክሰኞ፣ ኅዳር 25 2011

አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በመጪው ምርጫ በ547 ወረዳዎች ዕጩዎቹን ለማቅረብ መዘጋጀቱን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ተናገሩ።ንቅናቄው በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በንቃት የሚያሳትፍ ድርጅት ሊመሰርት መዘጋጀቱንም አቶ አንዳርጋቸው ጨምረው ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/39Nct
Äthiopien Ginbot 7 Meeting
ምስል Hanna Demisse

አርበኞች ግንቦት ሰባት

አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በመጪው ምርጫ በ547 ወረዳዎች ዕጩዎቹን ለማቅረብ መዘጋጀቱን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ተናገሩ። አቶ አንዳርጋቸው ይኸን ያሉት ንቅናቄው በብሪታኒያ እና አካባቢዋ ከሚገኙ አባላቱ ጋር በመከረበት ስብሰባ ላይ ነው። ንቅናቄው በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በንቃት የሚያሳትፍ ድርጅት ሊመሰርት መዘጋጀቱንም አቶ አንዳርጋቸው ጨምረው ተናግረዋል። አዲስ የሚቋቋመው ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ እና መርሐ-ግብር በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ዝግጁ ይሆናሉም ተብሏል። በትናንትናው ዕለት በለንደን ከተማ የተካሔደውን ውይይት የተከታተለችው ሃና ደምሴ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።


ሃና ደምሴ


እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ