1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አማጽያንን ትጥቅ የማስፈታቱ ርምጃ

ዓርብ፣ ግንቦት 26 2014

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በሰላማዊ መንገድ እጅ የሰጡ እና የተሀድሶ ስልጠና የወሰዱ ከአንድ ሺህ በላይ ታጣቂዎችን በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ለማሠራት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/4CFml
Karte Äthiopien Metekel EN

«በሰላማዊ መንገድ እጅ የሰጡ ታቂዎች ናቸው»

የክልሉ ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሀሚድ በዞኑ ሰላም ለማሰፈን በተሰሩ ሥራዎች የተሻለ ውጤት ተገኝቷል ብለዋል። በቅርብ በሰላማዊ መንገድ እጅ የሰጡ ከ400 ለሚሆኑ ወጣቶች ደግሞ የተሀድሶ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በካመሺ ዞን ደግሞ ከዚህ ቀደም እርቅ ተፈጽሞ ወደ ሰላማዊ መንገድ ተመልሰናል ያሉ የተወሰኑ ግለሰቦች ትጥቅ አንፈታም በማለት ግጭት ለመፍጠር ሲንቅሰቀሱ ተስተውሏል ብለዋል።

ነጋሳ ደሳለኝ 

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ