1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሌ ልዩ ወረዳ «ታጣቂዎች» ባደረሱት ጥቃት  አምስት ሰዎች ተገደሉ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 18 2014

በደቡብ ክልል አሌ ልዩ ወረዳ «ታጣቂዎች» ባደረሱት ጥቃት  አምስት ሰዎች ተገደሉ ። ለጊዜው ማንነታቸው በውል ያልተገለጸ ታጣቂዎች ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በሶስት ቀበሌዎች ዘልቀው በመግባት ሶስት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት አድርሰው መግደላቸውን በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/42Iik
Äthiopien Ale Wereda | Bürgergespräch nachdem 5 Menschen durch Waffengewalt starben
ምስል Ale Wereda Commuications office

በአሌ ልዩ ወረዳ ታጣቂዎች ያደረሱት ጥቃት

ለጊዜው ማንነታቸው በውል ያልተገለጸ ታጣቂዎች ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በሶስት ቀበሌዎች ዘልቀው በመግባት ሶስት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት አድርሰው መግደላቸውን በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል። ሁለቱ ሰዎች ደግሞ እርስ በእርስ ተታኩሰው መገዳደላቸው ነው የተነገረው። 

በታጣቂዎቹ ጥቃት ግድያ መፈጸሙን  ለዶቼ ቬለ (DW) ያረጋገጡት የአሌ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች በበኩላቸው በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ በፀጥታ ሀይሎች ክትትል እየተደረገ እንደሚገን ገልጸዋል

 ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ