1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትኩረት የሳበው የአውሮጳ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ

ዓርብ፣ መጋቢት 13 2016

የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ብራስልስ ለሁለት ቀናት ተካሂዶ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል፡፤ ጉባኤው በተለይ የዩክሬንንና መካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ በደረሰበትና በመጭው ስኔ ወር ከሚካሄደው የአውሮጳ ፓርላማ ምርጫ በፊትም የተካሄደ የመጨረሻ ጉባኤ በመሆኑ ልዩ ትኩረት የተስጠው ነው ተብሏል ።

https://p.dw.com/p/4e1xZ
የአዉሮጳ ህብረት ስብሰባ
የአዉሮጳ ህብረት ስብሰባ ምስል John Thys/AFP/Getty Images

ትኩረት የሳበው የአውሮጳ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ

የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከትናንት ጀምሮ እዚህ ብራስልስ ለሁለት ቀናት ተካሂዶ  ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል፡፤ ጉባኤው  በተለይ  የዩክሬንንና መካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ በደረሰበትና በመጭው ስኔ ወር ከሚካሄደው የአውሮጳ ፓርላማ ምርጫ በፊትም የተካሄደ የመጨረሻ ጉባኤ  በመሆኑ ልዩ ትኩረት የተስጠው ነው ተብሏል ።

ለዩክሬን የተወስነው አዲስ እርዳታ
የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ጀመሮ የአውሮፓ ህብረት በቢልዮን የሚቆጠር የገንዘብና የጦር መሳሪያ የለገሰ ቢሆንም፤ ጦርነቱ ግን በተለይ በዩክሬን በኩል ብዙም ያልገፋ በመሆኑና ይልቁንም  ዩክሬን  የተመጣጠነ የጦር መሳሪያና ተተኳሽ እጥረት ያጋጠማት መሆኑን በመግለጽ እያሰማች ባለው ጥሪ፤ የአውሮፓ ህብረትና አባል አገራቱተጨማሪ የእርዳታ ምንጮችን ሲያፈላልጉ እንደከረሙ ነው ሲዘገብ የቆየው። በተለይ ከአሜሪካ የሚጠበቀው ከፍተኛ መጠን ያለው እርዳታ ገና ያልተለቀቀ መሆኑ የጉዳዩን አሳስቢነትና አጣዳፊነት አሳድጎት ቆይቷል። በዚህ ላይ በተደረገው ውይይት የህብረቱ መሪዎች ጠቃሚና ወሳኝ የተባለ  ውሳኔ ያስተላለፉ መሆኑን የካውንስሉ ፕሬዝድትና የሰብሰባው መሪ ሚስተር ሚሸል በስጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። “ ከሩሲያ ተቀማጭ ገንዘብ የሚገኘው ትርፍ ለዩክሬን እንዲሰጥ የሚያደርግ ጠቃሚ ውሳኔ አስተላልፈናል ። ከዚህ በሚገኘው ገንዘብ ዩክሬንን በጦር መሳሪያ ለመርዳት ቁርጠኞች ነን፤ በማለት 27ቱም የህብረቱ መሪዎች የጉዳዩን አሳስቢነት እንደተረዱትም አስታወቀዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮላድሚር ዜሌንስኪ
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮላድሚር ዜሌንስኪምስል Ukrainian Presidency via abaca/picture alliance


በአውሮፓ ባንኮች የታገደው የሩሲያ ገንዘብና ትርፉ
በአውሮፓ ባንኮች 210 ቢሊዮን ኢሮ የሚደርስ የሩስያ ገንዘብ ታግዶ የሚገኝ ሲሆን፤ ክዚህ ገንዘብ የሚገኘውና በአመት 3 ቢሊዮን ኢሮ የሚደርሰው ትርፍ ነው ወደ ዩኪረን እንዲተላለፍ የተወሰነው።  ሩሲያ ሀሳቡን አስቀድማ እንደታቃወመችና የህግ ክርርክር ሊያስነሳ እንደሚችል ቢታወቅም ገንዘቡ ግን ቢዘገይ በሚቀጥለው ሀምሌ ወር ሊላክ እንደሚችል የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ  ቮንዴርሌየን ክሚስተር ሚሸል ጋር በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።
የመሪዎቹ ጉባኤ በጋዛ ሰባዊ ቀውስ ላይ  ያስተላለፈው ውሳኔ   
በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም በጋዛ ስላለው ሰባዊ ቀውስና እረሀብም መሪዎቹ ክዚህ ቀደም ባልታየ  ሁኒታ  በአንድነት ጠንካራ ውሳኔ ያስተላለፉ መሆኑ ተገልጿል። ሚስተር ሚሸል በመግለጫቸው፤  በጋዛ ጉዳይ፤ ጉባኤው ጠንካራና  ጠቃሚ መልክት አስተላለፏል በማለት ህብረቱ የሃማስን አሸባሪ ድርጊት እንዳወገዘና እንደሚያወግዝ ሁሉ በጋዛ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውንም እንደሚያወግዝና ሰባዊ እርዳታም በፍጥነት እንዲገባ የጠየቀ መሆኑን አስታውቀዋል፤ “ የሰባዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኞች ነን። ዛሬ በጋዛ የሚታየው ሰባዊ ትራጀዲ ነው። ለተቸገሩ እርዳታ ሊደርስ በሚችልበት ሁኒታ የበኩላችንን ማድረግ እንዳለብ እናምናለን”፤ በማለት ለዚህም የመሪዎቹ ስምምነት መኖሩን ገልጸው፤ እስራኤል በራፋ ወታደራዊ ዘመቻ እንዳታካሂድም ጥሪ የተላለፈ መሆኑን አስታውቀውል።  
ይህ የአውሮፓ ህብረት ውሳኔ  እስራኤል የሀማስን የመስከረም 26 የሺብር ጥቃት ተከትሎ በጋዛ ላይ በአየርና በምድር ጦርነት ከከፍተች 166 ቀናት በኋላ በሙሉ ድምጽ የተላለፈ ጠንካራ ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል። በጋዛ አሁን ያለው ሁኔታ የክፋና በሺዎች የሚቆጠሩ በጠኔ ተይዘው ከሞት አፋፍ ላይ ያሉበት መሆኑን የመንግስትቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽም በጉባኤው ዕለት እዚህ ብራስልስ ተገንተው፤ “ ዛሬ በጋዛ ካንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ  በጠኔ ተይዞ በሞት አፍፍ ላይ ነው የሚገኘው፡ በማለት ፈጥኖ መድረስ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል
አሚሪካም ዛሬ በመንግስታቱ ድርጅት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ የሚጠይቅ የውሳኔ  ሀሳብ ማቅረቧ የተነገረ  ሲሆን፤  ይህ የህበረቱ ውሳኔ ከዚህ የአሜርካ የአቋም ለወጥ ጋር የተገናኘ ይሁን አይሁን ባይታወቅም፤ ሁሉም ግን በጋዛና እስራኤል ላይ የአቋም ለውጥ ማድረጋቸውን  የሚያመላክት ነው እየተባለ ነው። 


ገበያው ንጉሴ 
 
አዜብ ታደሰ 
ታምራት ዲንሳ