ተቃውሞ በትግራይ ክልል
ማክሰኞ፣ ግንቦት 18 2012ማስታወቂያ
በትግራይ ክልል ወጀራትና አስገደ ወረዳዎች እንደ አዲስ ከተደራጁ ወረዳዎች ማዕከልነት ጋር በተያያዘ ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን እየገለፁ ነው፡፡ በክልሉ አስገደ ወረዳ ማይ ሓንሰ ነዋሪዎች በዚሁ ቅሬታ ከአካባቢያቸው ወደ ሽረ የሚወስደውን መንገድ ዘግተዋል፡፡በወጀራትም የወረዳው ማዕከል ወደ ሌላ አካባቢ ተወስዷል የሚል ቅሬታ ያላቸው ነዋሪዎች እሁድ በሰልፍ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል። ዶቼቬለ ለነዚህ ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የወረዳዎቹ ባለሥልጣናት መልስ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።ዝርዝሩን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ከመቀሌ ልኮልናል።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ