1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃዋሚው ባይቶና በትግራይ ሁሉን አካታች ምክር ቤት እንዲቋቋም ጥሪ አቀረበ

ዓርብ፣ መስከረም 24 2017

ባይቶና "ግዚያዊ አስተዳደሩ ሐላፊነቱን መተግበሩ አለመተግበሩን መከታተል የሚቻለው ምክርቤት ሲኖር ነው"ይላል።የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የስራ አፈፃፀሙን፣ በጀት እና ዕቅድ የሚከታተል የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪል ማሕበራት እና ሌሎችን ያካተተ ምክርቤት ለማቋቋም ባለፈው ዓመት አዋጅ አጽድቋል። ምክርቤት ግን እስካሁን ወደ ስራ አልገባም።

https://p.dw.com/p/4lQRt
Äthiopien Mekelle City Tigray
ምስል Million Hailesilassie/DW

በትግራይ ሁሉን አካታች ምክር ቤት እንዲቋቋም ተቃዋሚው ባይቶና ጥሪ አቀረበ

በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው እና በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላት የሚያሳትፈው የታላቋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ባይቶና እንደሚለው በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሰረት የተቋቋመው የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር የሚከታተል ምክርቤት እንዲቋቋም ጠይቋል። ግዚያዊ አስተዳደሩ በርካታ ሐላፊነቶቹne በሚገባ እየተወጣ አይደለም የሚለው ባይቶና፥ ይህን ለመፍታት እና ተጠያቂነት ለማረጋገጥ ሁሉን አካታች ምክርቤት እንዲቋቋም ጥሪ አቅርቧል።
የባይቶና ሊቀመንበር አቶ ክብሮም በርሃ "ግዚያዊ አስተዳደሩ ሐላፊነቱን መተግበሩ አለመተግበሩ መከታተል የሚቻለው ምክርቤት ሲኖር ነው" ይላሉ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የስራ አፈፃፀሙ፣ በጀት እና ዕቅድ የሚከታተል የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪል ማሕበራት እና ሌሎች ያካተተ ምክርቤት ለማቋቋም ባለፈው ዓመት አዋጅ ማፅደቁ ይታወሳል። ሕወሓት ብቻውን ትግራይን ወክሎ መደራደር የለበትም መባሉ

ይህ ተከትሎ ከሰባት ወራት በፊት ማብራሪያ ሰጥተው የነበሩት በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በምክትል ፕሬዝደንት ማዕርግ የዴሞክራታይዜሽን እና ያልተማከለ አስተዳደር ዘርፍ ሐላፊ ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ የሚቋቋመው ምክርቤት ሁሉ አካታች እና የመወሰን ስልጣን ያለው ብለውት ነበር። ይሁንና ይህ "በቅርቡ ይቋቋማል" ተብሎ የነበረው ምክርቤት እስካሁን ወደ ስራ አልገባም።ሕወሓት ብቻውን ትግራይን ወክሎ መደራደር የለበትም መባሉ
ለዚህ የምክርቤቱ መቋቋም መዘግየት አልያም አለመተግበር ባይቶና ግዚያዊ አስተዳደሩ እና ህወሓትን ተጠያቂ አድርጓል። በዚህ ጉዳይ ዙርያ ከትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የሚመለከታቸው የስራ ሐላፊዎች ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልሰመረም።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ