ብሪታንያ የአውሮጳ ህብረትን የምትለቅበት ስምምነት ጉዳይ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 30 2011ላለፍት ሁለት ዓመታት በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ እንደተሰማው፣ የብሪታንያ እና የአውሮጳ ህብረት ፍች በቀጥታ አልያም በተዘ ዋዋሪ ከሚፈጥረው የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያው ጊዚያዊ ጫና የሚያመልጥ ሀገር አይኖርም።ባንድ ወቅት ታላቅዋ ብሪታንያ ከአውሮጳ ህብረት ትወጣለች የሚለው ሀሳብ እውን ይሆናል ማለት የማይታሰብ ነበር፣ ነገር ግን የፓለቲካ ድል ለማግኝት ሲሉ ምርጫውን የፈቀዱት የቀድሞው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ዲቪድ ካምረን ከሁለት አመት በፊት ህዝባቸው ድምፅ ችንዲሰጥበት የወሰኑት ከህብረቱ እንውጣ አንውጣ የሚለው ውሳኔአቸው ሀገራቸውን ከአውሮጳ ህብረት፣ እሳቸውን ከስልጣንቸው ካስወጣ በኋላ ጉዳዩ እስካሁን መነጋገሪያ ፣መነታርኪያ፣ ጣት መጠቆዋቆሚያ እና ማስፍራሪያ ሆኗል። ብሪታንያ ከህብረቱ ጋር ለ45 ዓመት አብራ ከኖረች በኋላ አሁን ከህብረቱቱ ለመለያየት ያቀረበችው የፍቺ ሰነድ እሰከዛሬ አብረዋት የቆዩት 27 ቱ አባል አገሮች በሙሉ የሚስማሙበት መሆን አለበት፣ ከዚህ በተጨማሪም ሰነዱ የብሪታንያን ፓርላም ተቀባይነት ማግኘት አለብት ።
በብሪታንያ ትላንት 200 በላይ የሚሆኑ ብሬግዚትን የሚደግፍ እና የማይደግፉ የፓርላማ አባላት ጭምር ለጠቅላይ ሚንስትር ተሪዛ ሜይ ብሪታንያ ያለ ስምምነት የአውሮጳ ህብረትን እንዳትለቅ ደብዳቤ ልከዋል። 585 ገፅ የያዘው የፍቺ ሰነደ በአውሮጳ ህብረት ዘንድ የመጨረሻው የስምምነት ዶስየ እንደሆነ ተነግሮዋል ።
ሜይ ያቀረቡት ይህ ባለብዙ ገፅ ሰነድ ከአንድ ሳምንት በኋላ በብሪታንያ በፓርላማ ድማፅ ይሰጥበታል። የፓርላማውን ተቀባይነት ካገኛ ከ60 ቀናት በሁዋላ መጋቢት 20 ብሪታንያ ከአውሮጳ ህብረት በይፋ የምትወጣበት ሰነድ ይሆናል ማለት ነው ።
ጥናት እና ምርምራቸውን ላለፉት 11 አመታት በምህንድስና ላይ ያደረጉት ዶክተድ በላቸው ጨከነ ተስፋ በብሪታንያ የጃግዋር ላንድሮቨር መኪና ማምረቻ መሪ መሀንዲስ፥ የብሪታንያ እና የአውሮጳ ህብረት ፍች ስለሚያስከትለው ችግር ከ«DW» ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተል።
ሀና ደምሴ
አርያም ተክሌ