1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም እና ኢንቨስትመንት

ዓርብ፣ የካቲት 29 2016

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በስድስት ወራት ውስጥ ለ188 አዳዲስ ባለሀብቶች በግብርና ዘርፍ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ። ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዙ የኢንቨስትመንት ስራ ቀንሶ እንደነበር ገልጸው በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም እየሰፈነ በመሆኑ ባለሀብቶች ወደ ስራ እየገቡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4dJRi
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ግልገል በለስ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ግልገል በለስምስል Negassa Desalegn/DW

ባለሀብቶች የወሰደቡትን መሬት ባግባቡ ማልማት አለባቸው

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በስድስት ወራት ውስጥ ለ188 አዳዲስ ባለሀብቶች በግብርና ዘርፍ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ። የክልሉ የመሬትና የህብረት ስራ ማደረጃ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም መንጌሻ ፈቃድ የተሰጣቸው ባለሀብቶች በክልሉ አሶሳ እና መተከል ዞን ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገቡ ተቁመዋል። ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዙ የኢንቨስትመንት ስራ ቀንሶ እንደነበር ገልጸው በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም እየሰፈነ በመሆኑ ባለሀብቶች ወደ ስራ እየገቡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።


በክልሉ በግብርና ዘርፍ ፈቃድ የወሰዱ 976 ባለሀብቶች ይገኛሉ


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ለረጀም ጊዜ በነበረው አለመረጋጋትሳቢያ የኢንቨስትመንት ስራዎች በተለያዩ አካባቢዎች ተቀዛቅዞ እንደነበር የክልሉ የመሬትና ህብረት ስራ ማደረጃ ቢሮ ገልጸዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመሬትና ህበረት ስራ ማህበራዊ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም መንጌሻ በአሁኑ ወቅት በአሶሳ እና መተከል ዞን ውስጥ 188 አዳድስ ባለሀብቶች በእርሻ ኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ፈቃድ እንደተሰጣቸውን ገልጸዋል።
በመተከል ዳንጉርናጉባ የተባሉ ወረዳዎች እንዲሁም በአሶሳ ዞን ባምባሲ እና አብራሞ የተባሉ አካባቢዎች ባለሀብቶች በእርሻ ዘርፍ የሚሳተፉባቸው አካባቢዎች እንደሆኑም አመልክተዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት ፈቃድ በመውሰድ በጸጥታ ችግር ምክንያት ስራ ያቋረጡ ወይም ወደ ስራ ሳይገቡ የቆዩ ባለሀብቶችም እንደነበሩ ገልጸው ባጠቃላይ ሰላም በሰፈነባቸው አካባቢዎች 976 ባለሀብቶች በእርሻ ኢን,ቨስትመንት ይገባሉ ብሏል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ግልገል በለስ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ግልገል በለስምስል Negassa Dessalegn/DW


ባለሀብቶች የወሰደቡትን መሬት ባግባቡ ማልማት አለባቸው
ወደ ስራ የሚገቡ ባለብቶች የወሰዱትን መሬት በአግባቡ በማልማት፣ የስራ ዕድል መፍጠርና የአካባቢውን ማህበረሰብም እንደዚሁ ተጠቃሚ ማድረግ አለባቸው ብሏል። ከዚህ ቀደም መሬት ወሰደው በአግባቡ ሳያለሙ ለዓመታት የቆዩም ባለብቶች እንደነበሩ ጠቁሟል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የካቲት 11/2016 ዓ.ም ባቀረቡት ዘገባ እንዳስታወቁት በክልሉ በግብርና ዘርፍ ለውጥ መመዝገቡን እና ግብርናን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ለባለሀብቶች ፈቃድ መሰጡትን አስታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ የተወሰኑ ባለሀብቶች ፈቃድ መሰረዙንም ጠቁሟል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከ1ሺ በላይ ባለሀብቶች በግብርና ማዕድን ዘርፍ ተሰማርቶ እንደሚገኙ ተገልጸዋል። በክልሉ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰቱትየጸጥታ ችግሮች ምክንያት ባለሀብቶች በተለያዩ አካባቢዎች ወደ ስራ ሳይገቡ መቆየታቸውን የክልሉ መሬትና ህብረት ስራ ማደረጃ ቢሮ መረጃ ያመለክታል።


ነጋሳ ደሳለኝ 
አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ