ባል እንደአዋላጅ | ጤና እና አካባቢ | DW | 15.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

ባል እንደአዋላጅ

ዘመናዊነትን የተከተለው የእናቶች ቀን ሲከበር ምዕተ ዓመት እንደደፈነ መረጃዎች ያመለክታሉ። የዚህ የዘመናዊ የእናቶች ቀን መታሰቢያ ዕለት የሃሳብ ጠንሳሽ የሆኑት አሜሪካዊት በወቅቱ ፀረ ጦነርነት አቋማቸውን ያንጸባረቁበት እንደሆነ ቢነገርም ውሎ አድሮ ግን የንግድ ማድመቂያነቱን በይፋ መቃወማቸው ይነገርላቸዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:17

ነፍሰጡር እናቶች የባሎቻቸውን ትኩረት ይሻሉ

ከዚህ ባሻገር ግን ዘጠኝ ወር በሆዷ ተሸክማ በምጥ ታምማ ወደዚህች ምድር ለምታመጣ፤ እንዲሁም ልጇ ሲታመም እየታመመች ለምታሳድግ ድንቅ ፍጥረት መታሰቢያ የሆነው ቀን ዋጋ ሊሰጠው እንደሚገባ ብዙዎች ይስማሙበታል። ባሳለፍነው እሁድ ይህ ቀን በብዙ ሃገራት ታስቧል። ይህ ምስጋና የሚገባቸው አባቶች መኖራቸው ሳይዘነጋ እናቶችም ነፍስ ካወቁ ልጆቻቸው ምስጋናን አግኝተዋል። እናትነቱ ሲታሰብ የመውለዱ ሂደት ይታወሳል እና ባለፈው ሳምንት ባለቤታቸውን እንዳዋለዱ የጠቆሙንን አድማጭን ታሪክ ልናካፍላችሁ ቀጠሮ ነበረን። በዚህ በምዕራቡ ዓለም ነፍሰጡር ሚስቶች ልጆቻቸውን ሊገላገሉ ሀኪም ቤት ሲገቡ ባሎች ከጎንሆነው ልጁ እንዲወለድ ሚስቶቻቸውን ያበረታሉ አጽናናሉ። የእኝህኛው ገጠመኝ ግን ከዚህ ይለያል። ራሳቸው ናቸው ባለቤታቸውን ያዋለዱት። ዝርዝሩን ከድምፅ ዘገባው ይከታተሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic