በፈረንሳይ የቀጠለው ተቃውሞ
ቅዳሜ፣ ኅዳር 29 2011ማስታወቂያ
ተቃዋሚዎቹ ከፖሊስ ጋር የተጋጩ ሲሆን ሦስት ፖሊሶችን ጨምሮ ከ30 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የፈረንሳይ ባለሥልጣናት 8,000 ሰዎች መሳተፋቸውን የገለጡ ሲሆን 600 ያህል መፈተሻቸውን እና ለአጭር ጊዜም ቢሆን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቀዋል። በዛሬው ዕለትም ከተማዋ የተለመደ እንቅስቃሴዋ ርቋት እንደዋለች የገለፀችልን የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ፤ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ተቃውሞ ከሚያካሂዱት ፈረንሳውያን ጋር እንደሚነጋገሩ ባለስልጣናት ማመልከታቸውን ገልፃልናለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ