1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጂማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ በታጣቂዎች ደርሷል የተባለው ጥቃት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 20 2013

በኦሮሚያ ክልል ጂማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ በንጹሐን ዜጎች ላይ በታጣቂዎች የደረሰውን ጥቃት በስፍራው ተገኝቶ ለማጣራት አለመቻሉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3shKx
Karte Äthiopien englisch

«የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በስፍራው ተገኝቶ ማጣራት አልቻለም»

 

በኦሮሚያ ክልል ጂማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ በንጹሐን ዜጎች ላይ በታጣቂዎች የደረሰውን ጥቃት በስፍራው ተገኝቶ ለማጣራት አለመቻሉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ዓርብ ሚያዚያ 15 ቀን 2013 በደረሰው ጥቃት ሲቪል ዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱን ቢያረጋግጥም፤ እስካሁን መርማሪ ቡድኑን ወደ ስፍራው ለመላክ አስቻይ ሁኔታ አለመኖሩን ገልጿል። ሆኖም በደረሰው ጉዳት ንጹሐን መጠቃታቸውን ኮሚሽኑ ከአከባቢው ነዋሪዎችና ከተጎጂ ቤተሰቦች ማረጋገጡም ተነግሯል። አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የኢ.ሰ.መ.ኮ. የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች አማካሪ ኢማድ አብዱልፈታ ከጥቃቱ በኋላ በስፍራው የደረሱት የክልልና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ሊደርስ የነበረውን ተጨማሪ ጉዳት ማስቆማቸውን ኮሚሽኑ ተረድቷል ብለዋል። በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ የተደረገላቸው የዞንና የክልል የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ግን ምላሽ ሳይሰጡበት ቀርተዋል።

ስዩም ጌቱ 

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ