በደሴ የሙሲሊሞች መታሰር  | አፍሪቃ | DW | 19.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

በደሴ የሙሲሊሞች መታሰር 

በደቡብ ወሎ ደሴ ከተማ ባለፉት 20 ቀናት ዉስጥ ከጎሮ አስዋር መስጂድ ብዙ ሰዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መያዛቸዉን በአከባብዉ የሚኖሩ አድማጮች ለዶቼ ቬሌ የላኩት ጥቆማ ያመለክታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:49

ከጎሮ አስዋር መስጂድ ብዙ ሰዎች ተይዘዋል

በደቡብ ወሎ ደሴ ከተማ ባለፉት 20 ቀናት ዉስጥ ከጎሮ አስዋር መስጂድ ብዙ ሰዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መያዛቸዉን በአከባብዉ የሚኖሩ አድማጮች ለዶቼ ቬሌ የላኩት ጥቆማ ያመለክታል። የአካባቢዉ ነዋሪ መሆናቸዉን የገለፁልን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ  «60» የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪ የእስልምና እምነት ተከታዮች ተይዘዉ ደሴ ወደ ሚገኘዉ ማረሚያ ቤት መወሰዳቸዉን ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

የሃይማኖት አክራርነት መሰረት ያደረጉ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ሆኖም ግን በከተማዋ አለመረጋጋትም ይሁን የኅብረተሰቡን የእለተእለት እንቅስቃሴ የሚያዉክ ነገር እንደሌለ በአማራ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሼን ኃላፍ የሆኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁን  ለዶቼ ቬሌ ገልጸዋል።

ስለታሳሪዎቹ ሁኔታ አሁን መረጃ እንደሌላቸዉ የገለፁት አቶ ንጉሡ የክሳቸዉ ዝርዝር በሕግ ስረዓት ተከትሎ ወደ ፊት ይገለፃል ይላሉ። የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥታት በሃይማኖት ጉዳዮች ዉስጥ ታልቃ ይገባሉ የሚል ክስ የሚያሰሙ ወገኖች አሉ።

ከአራት ወይም አምስት ዓመት በፊት የሃይማኖት አባቶች መገደላቸዉንና እሱም አሁን በፍርድ ሂደት ላይ እንደሚገኝም አቶ ንጉሡ ጨምረዉ ተናግረዋል። 

ለበለጠ መረጃ ኡዉዲዮዉን ያዳምጡት።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic