1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኦሮሚያ ከተሞች የተደረገዉ ሰልፍ

ዓርብ፣ ጥቅምት 26 2014

በየከሞቹ አደባባይ የወጣዉ ሕዝብ የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጃቸዉን ህዝባዊ ወያኔ ሐሪነት ትግራይ (ሕወሃት) እና የኦሮሞ ነጻነት ጦር (ኦነግ ሸኔ)ን አዉግዟል። ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለመስጠትም ቃል ገብቷል።

https://p.dw.com/p/42dwP
Äthiopien | Proteste gegen OLA und TPLF
ምስል Seyoum Getu/DW

                     

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 19ኝ ከተሞች ዛሬ የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚደግፉ የአደባባይ ሰልፎች ተደረጉ። በየከሞቹ አደባባይ የወጣዉ ሕዝብ የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጃቸዉን ህዝባዊ ወያኔ ሐሪነት ትግራይ (ሕወሃት) እና የኦሮሞ ነጻነት ጦር (ኦነግ ሸኔ)ን አዉግዟል። ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለመስጠትም ቃል ገብቷል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ  በተለይ የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ጦር አዲስ አበባ አካባቢ መሽጓል እየተባለ የሚናፈሰዉ ዘገባ ፕሮፓጋንዳ በማለት አጣጥለዉታል። ተመሳሳይ ሰልፎች ይቀጥላሉ ተብሏልም።

 ስዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ