በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ሊቃነ ጳጳሳት ጥሪ | ኢትዮጵያ | DW | 17.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ሊቃነ ጳጳሳት ጥሪ

ሊቃነ ጳጳሳቱ ለአሜሪካ መንግስት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እና ሌሎች ባለስልጣናት በፃፉት ደብዳቤ ዩናይትድስቴትስ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ አስመልክቶ ይዘዋለች ያሉት አቋም ስጋት ያሳደረባቸው መሆኑን ገልፀዋል። የደሕንነት እና ፍትኅ ለትግራይ ምክትል ፕሬዝደንት "የአሜሪካ መንግሥት አቋም ግልጽ ነው።እንደግፈዋለን" ብለዋል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:18

የሰሜን አሜሪካ ሊቃነ ጳጳሳት ጥሪ

ዩናይትድስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችው አቋም አሳስቦናል ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ አስር ሊቃነ ጳጳሳት አመለከቱ። ሊቃነ ጳጳሳቱ ለአሜሪካ መንግስት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እና ሌሎች ባለስልጣናት በፃፉት ደብዳቤ ዩናይትድስቴትስ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ አስመልክቶ ይዘዋለች ያሉት አቋም ስጋት ያሳደረባቸው መሆኑን ገልፀዋል።በአሜሪካና በካናዳ የሚገኙ የ11 አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ትናንት ከአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎችና አማካሪዎቻቸው ጋር ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በጉዳዩ ላይ  ተወያይተዋል።ሊቃነ ጳጳሳቱን ወክለው የኒውዮርክና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቃነጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ለዶይቸ ቨለ በሰጡት መግለጫ በትናንቱ ውይይት በጎ ምላሽ መገኘቱን ተናግረዋል።

Logo Security and Justice for Tigrayans

ደሕንነት እና ፍትኅ ለትግራይ

የደሕንነት እና ፍትኅ ለትግራይ ምክትል ፕሬዝደንት ፕሮፈሰር ሙሉጌታ ገብረእግዚዓብሔር በበኩላቸው "የአሜሪካ መንግሥት አቋም ግልጽ ነው። እኛም እንደግፈዋለን።" ሲሉ ተናግረዋል። ፕሮፈሰር ሙሉጌታ ለዶይቼ ቬለ "አንዱ የአሜሪካ መንግሥት እያለ ያለው ነጻ የሆነ ዓለም አቀፍ አካል ምርመራውን ያካሒደው ነው የሚለው። በዚህ ላይ ደግሞ የመንገዶች መዘጋት፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዳይገባ መከልከል፣ የመብራት መጥፋት፣ የስልክ መጥፋት፣ የቴሌኮምዩንኬሽን አውታሮች መዘጋጋት እንዲነሳ ነው ጥሪ እያቀረቡ ያሉት" ብለዋል።


ታሪኩ ኃይሉ 
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች