1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ ለውጥ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

ማክሰኞ፣ መስከረም 5 2013

በኢትዮጵያ የገንዘብ ኖቶች ላይ የተደረገው ለውጥ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ብዙ የፋይናንስ ባላሙያዎች የሀገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት ፈር በማስያዝና የተናጋውን ኢኮኖሚ መልክ እንዲኖረው በማድረግ ረገድ በአዎንታ ተመልክተውታል።

https://p.dw.com/p/3iVNb
Äthiopien Währung Birr
ምስል DW/Eshete Bekele Tekle

በኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ ለውጥ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

በኢትዮጵያ የገንዘብ ኖቶች ላይ የተደረገው ለውጥ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ብዙ የፋይናንስ ባላሙያዎች የሀገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት ፈር በማስያዝና የተናጋውን ኢኮኖሚ መልክ እንዲኖረው በማድረግ ረገድ በአዎንታ ተመልክተውታል።
አንዳንዶች ደግሞ የሁለት መቶ ብር ኖት መታተሙ መልካም ቢሆንም የተቀረው ማሻሻያ የተለየ እመርታዊ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ስለማምጣቱ ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል። ይልቁንም ያልተጠበቀ ትርምስ ፈጥሮ የባሰ የዋጋ ንረት እንዳያስከትል ስጋታቸውን ጠቅሰዋል።
ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ የገንዘብ ጥቁር ገበያ ልውውጥ በስፋት በሚስተዋልበት በስታዲየምና ብሔራዊ ቴአትር አካባቢ በፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች ከፍተኛ ጥበቃ እና ቁጥጥር ሲደረግ እንደዋለ የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ ተመልክታል። ጥቂት ሰዎችንም በብር ለውጡ ዙሪያ አነጋግሯል።

ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ