1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት የተከሰተ የተማሪዎች ግጭት

ሰኞ፣ መጋቢት 5 2014

በአንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ሌሊት በተማሪዎች መካከል በተፈጠረው ብሔርን መሰረተ ያደረገ ግጭት በርካታ ተማሪዎች መጎዳታቸውን የአይን እማኝ ተማሪዎች ለዶይቼ ቬለ ገለፁ፡፡ አስተያየታቸውን የሰጡን ተማሪዎቹ እንደሚሉት ችግሩ ከተፈጠረ ቀናት ቢቆጠሩም በትናንትናው እለት ግን ወደ አካላዊ ግጭት መሸጋገሩን ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/48Sst
Äthiopien Addis Abeba University
ምስል Seyoum Getu/DW

ግጭቱን ያነሳሱት የተባሉት በቁጥጥር ስር ናቸዉ

በአንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ሌሊት በተማሪዎች መካከል በተፈጠረው ብሔርን መሰረተ ያደረገ ግጭት በርካታ ተማሪዎች መጎዳታቸውን የአይን እማኝ ተማሪዎች ለዶይቼ ቬለ ገለፁ፡፡ አስተያየታቸውን የሰጡን ተማሪዎቹ እንደሚሉት ችግሩ ከተፈጠረ ቀናት ቢቆጠሩም በትናንትናው እለት ግን ወደ አካላዊ ግጭት መሸጋገሩን ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ ግጭት ቀስቅሰዋል ያሏቸውን የፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው አመልክቷል ።

ለደህንነቱ ስባል ስሙ እንዳይጠቀስ ጠይቆ አስተያየቱን የሰጠን አንድ የዩኒቨርሲቲው ተማሪ እና የአይን እማኝ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገረው፤ በዩኒቨርሲቲው ትናንት ብሔርን መሰረት አድርጎ ለተቀሰቀሰው ግጭት ምክኒያት የነበረው ይህ ነው ይላል፡፡ ችግሩ ከተጠነሰሰ 10 ቀናት ተቆጥረዋል የሚለው ይህ ተማሪ፤ ከዚህ በፊት የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች የካቲት 26 የተበተነውን የጥላቻ ወረቀት ተቃውመው ሰልፍ ከወጡ በኋላ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ሌላ ሰልፍ የካቲት 29 ይወጣሉ፡፡

አስተያየቱን የሰጠን ሌላው የዩኒቨርሲቲው ተማሪም የግጭቱ መነሻ የተበተነው ጥላቻን የሚሰብክ ወረቀት ነው ይላል፡፡ ተማሪዎቹ በአስተያየታቸው ዩኒቨርሲቲው ችግሩን ከመሰረቱ ፈቶ ሰላማቸውን እንዲያስጠብቅላቸውም ጠይቀዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ ግጭቱን ያነሳሱት በህግ ጥላ ስር መዋላቸውን ዛሬ አስታውቋል፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ኢንጂነር ውባቸው ማሞ እንዳሉት ቀደም ሲል ተማሪ የነበሩና አሁን ተማሪ ያልሆኑ ወደ ጊቢው ገብተው ተማሪዎችን የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃ ለማድረግ ሰርተዋል ነው ያሉት፡፡ የመማር ማስተማሩ ሂደት ግን መልሶ መቀጠሉንም አመልክተዋል፡፡

 

ስዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ