በአማሮ ወረዳ የ12 ሰዎች ህይወት ያጠፋው ጥቃት ሺዎችን አፈናቅሏል
ማክሰኞ፣ መጋቢት 28 2013ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች የታጠቁ ቡድኖች በተለያዩ ቀናት በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች ተገድለው፣ ከ11 ሺ በላይ መፈናቀላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ታጣቂዎቹ እያደረሱ ባለው ጥቃት ፣ ግድያና ዘረፋ ህልውናችን በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለተናግረዋል። ታጣቃዊዎቹ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በልዩ ወረዳው የተለያዩ ቀበሌያት በመዘዋወር ባደረሷቸው ጥቃቶች በሰዎች ላይ ካደረሷቸው ግድያ በተጨማሪ በንብረትም ላይ እያደረሱ ባለው ውድመት የመኖርያ ቄዬአቸውን ለቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን ነዋሪዎች ጨምረው ገልጸዋል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ