1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል የአመራር ለውጥ መታቀዱ

ረቡዕ፣ ግንቦት 7 2011

በአማራ ክልል መዋቅራዊ ለውጥ እስካልመጣ ድረስ የሹማምንት መቀያየር የሚለውጠው ነገር እንደማይኖር ምሁራን አመለከቱ። ምሁራኑ በተለይ ለዶይቼ ቬለ DW በሰጡት አስተያየት  የአመራር ምደባው በዕውቀት ላይ ሲመሠረት ብቻ ውጤት ሊመጣ እንደሚችል አስገንዝበዋል።

https://p.dw.com/p/3IYNt
Dr. Ambachew Mekonnen
ምስል DW/A. Mekonnen

መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚያስፈልግ ምሁራን አመላክተዋል

ከሰሞኑ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በቅርቡ የተደረገው የአመራር ለውጥ እና ድልድል የተፈለገውን ውጤት በክልሉ ማምጣት እንዳላስቻለ በመጠቆም፤ አዲስ የአመራር ለውጥ እንደሚደረግ መናገራቸው ተሰምቷል።  የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅትን ጠቅሶ የአማራ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ ድረ ገፅ እንዳመለከተው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን  አዲስ የአመራር ድልድል ሊያደርጉ ነው። ለዚህም ዋናው ምክንያት በቅርቡ የተደረገው የአመራር ለውጥና ድልድል የተፈለገውን ውጤት በአማራ ክልል ማምጣት ባለመቻሉ እንደሆነ ርዕሰ መስተዳድር መናገራቸውን  ጽሑፉ አመልክቷል። ከዚህ በፊት የተደረጉ ምደባዎች ለምን ውጤታማ እንዳልሆኑ ምሁራን ለዶይቼ ቬለ DW ተናግረዋል።  በጉዳዩ ላይ የምሁራንን አስተያየት በማካተት ከባሕር ዳር ዓለምነው መኮንን ዘገባ ልኮልናል።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ