1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
የምግብ ዋስትናኢትዮጵያ

በአማራ ክልል ከ200 በላይ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ቢታቀዱም የተጀመሩት 92 ብቻ ናቸው

ቅዳሜ፣ የካቲት 30 2016

በአማራ ክልል ከታቀዱ 214 የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች የተጀመሩት 92 ብቻ መሆናቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። በመንግሥት የጸጥታ አስከባሪዎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሔደ የሚገኘው ግጭት የታቀዱ የመስኖ ሥራዎች ግንባታ ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ የአማራ ክልል የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳኝነት ፈንታው ተናግረዋል

https://p.dw.com/p/4dKwO
የአማራ ክልል የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳኝነት ፋንታው
በመንግሥት የጸጥታ አስከባሪዎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሔደ የሚገኘው ግጭት የታቀዱ የመስኖ ሥራዎች ግንባታ ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ የአማራ ክልል የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳኝነት ፋንታው ተናግረዋልምስል Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል ከ200 በላይ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ቢታቀዱም የተጀመሩት 92 ብቻ ናቸው

በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት እና ጦርነት በመስኖ ልማት ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩን የአማራ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አስታወቀ። በዓመቱ መገንባት ከነበረባቸው 214 ፕሮጀክቶች 30ዎቹ ብቻ ስራቸው መጠናቀቁን ቢሮው አመልክቷል፡፡

ዉጥረት በአማራ ክልል

የአማራ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዳኝነት ፈንታው ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በዓመቱ ለማከናወን ከታቀዱ 214 የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል የተጀመሩት 92 ብቻ ናቸው። ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት መጠናቀቅ የቻሉት ደግሞ 30 ፕሮጀክቶች ብቻ ናቸው ነው ያሉት፡፡

በአማራ ክልል የቀጠለዉ ዉግያ

ከጥናትና ዲዛይን አኳያም ቢሆን 78 ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ እቅድ ቢያዝም ማከናወን የተቻለው 6ቱን ብቻ እንደሆነ ነው ቢሮ ኃላፊው ያስረዱት፡፡
ከፌደራል መንግስት መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስቴር ጋር በጋራ ከሚሰሩ 5 ግዙፍ ፕሮጀክቶች (Mega Projects) መካከልም ስራቸውን መጀመር የተቻለው የሁለቱን ብቻ እንደሆነ ዶ/ር ዳኝነት ገልጠዋል፡፡

የአማራ ክልል የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ
የአማራ ክልል የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳኝነት ፋንታው “የጸጥታ መደፍረስ” ያሉት ግጭት በፌድራል መንግሥት በጀት ሊከናወኑ የታቀዱ የመስኖ ሥራዎች ላይ ጭምር አሉታዊ ተጽዕኖ አሳርፏል። ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ምክንያት ተሸከርካሪዎችን፣ ለመስኖ ስራ የሚሆኑ መሳሪያዎችን፣ ግብዐቶችን፣ ነዳጅና ሌሎች አስፈላጊ መሳሪያዎችን እንደልብ ማንቀሳቀስ ባለመቻሉ የመስኖ ስራዎችን መስራት እንዳልተቻለ ነው ያብራሩት፡፡

አማራ ክልል በረሀብ ሰዎች መሞታቸውን ተፈናቃዮች ተናገሩ

ጦርነቱና ግጭቱ በክልሉ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ያስከተለ መሆኑን የሰብአዊ መብት ተቋማት የገለፁ ሲሆን፣ የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ትናንት በሰጠው መግለጫ ደግሞ እስከ 15 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት በጦርነቱ ምክንያት ወድሟል፡፡

ዓለምነው መኮንን
እሸቴ በቀለ