በትግራይ የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ በድጋሚ ተስተጓጎለ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 30 2011ማስታወቂያ
ከትግራይ ክልል ሽረ ተነስተው ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ለመንቀሳቀስ የሞከሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ማእከላዊ ዕዝ አባላት በዛሬው ዕለት በህዝብ ተቃውሞ እንቅስቃሴያቸው መገታቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለDW ተናግረዋል፡፡ ነዋሪዎቹ እንደገለጹት 25 ኦራል ተብለው የሚታወቁ የመከላከያ ሰራዊት ትልልቅ መኪናዎች ከነጭነታቸው እንዲሁም አምስት የወታደራዊ መኮንኖች መኪናዎች ከጉዟቸው ተስተጓጉሏል፡፡ በክልሉ ከሳምንት በፊት ተመሳሳይ ክስተት የተስተዋለ ሲሆን በዚያ የሚኖሩ ዜጎች አሁንም የደህንነት ስጋት አለብን ይላሉ፡፡
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ተስፋለም ወልደየስ
አርያም ተክሌ