1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ ከምርጫ በኋላ ኮሮናን ያላገናዘበው ሰልፍ 

ረቡዕ፣ መስከረም 6 2013

ህወሓት በትግራይ በተደረገው ምርጫ ማሸነፉን ተከትሎ አባላቶቹና ደጋፊዎቹ በመቐለ እና በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች ዛሬ ጠዋት ሰልፍ ተካሄደ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ የተሳተፈባቸው እነዚህ ሰልፎች የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት መደረጋቸው በተለያዩ አካላት ተተችተዋል።

https://p.dw.com/p/3iYqf
Äthiopien Addis Ababa | TPLF Marsch nach Wahlsieg
ምስል Million Hailesilassie/DW

«ሰልፉ በተለያዩ ከተሞች ተካሂዷል»

ህወሓት በትግራይ በተደረገው ምርጫ ማሸነፉን ተከትሎ አባላቶቹና ደጋፊዎቹ በመቐለ እና በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች ዛሬ ጠዋት ሰልፍ ተካሄደ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ የተሳተፈባቸው እነዚህ ሰልፎች የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት መደረጋቸው በተለያዩ አካላት ተተችተዋል። የትግራይ ክልል ርዕሰ ከተማ መቐለ ጨምሮ ውቅሮ፣ ማይጨው፣ አላማጣ፣ ሽረ፣ ሑመራና ሌሎች በርካታ ከተሞች ዛሬ ሰልፍ ከተደረገባቸው አካባቢዎች መካከል ናቸው። ዛሬ ጠዋት ከ12 ሰዓት ጀምሮ በመቐለ ሐውልት ሰማእታት ግቢ በተደረገ ስነ ስርዓት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ለህዝባቸው መልእክት አስተላልፈዋል። በሌላ በኩል የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት በትግራይ በተደጋጋሚ ህዝባዊ ሰልፎች መደረጋቸው ተገቢ አይደለም በማለት ብዙዎች ይተቻሉ። የትግራይ ጤና ቢሮ ትላንት ባወጣው ዕለታዊ የኮረና ተሐዋሲ መዘርዝር በክልሉ በ24 ሰዓት ምርመራ ከተደረገላቸው 706 ተጠርጣሪዎች 162ቱ ተሐዋሲው ተገኝቶባቸዋል። እስካሁን በአጠቃላይ በትግራይ 5267 ሰዎች በምርመራ ኮረና ተሐዋሲ እንደተገኘባቸው የክልሉ ጤና ቢሮ መረጃ ያመለክታል።  

ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ