በቤኒሻጉል ጉሙዝ ተደጋጋሚ ጥቃት እልባት አላገኘም | ኢትዮጵያ | DW | 17.11.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በቤኒሻጉል ጉሙዝ ተደጋጋሚ ጥቃት እልባት አላገኘም

በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች በተስፋፋው የጸጥታ ችግር ትናንት የሰው ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ ተናገሩ፡፡ ትናንት ታጣቂዎች በድባጢ ወረዳ አንግቶክ፣ ቆርቃ፣ አልባሰ  እና ሙዛን በተባሉ ቦታዎች ጥቃት ማድረሳቸውን አሁንም የጸጥታው ኹኔታ  አሳሳቢ መሆኑንን ነዋሪዎች አብራርተዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:46

የሰው ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል

በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ  የተለያዩ ቀበሌዎች በተስፋፋው  የጸጥታ ችግር ትናንት የሰው ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ (DW)ተናግረዋል፡፡ በትናትው ዕለት ታጣቂዎች በድባጢ ወረዳ አንግቶክ፣ ቆርቃ፣ አልባሰ  እና ሙዛን በተባሉ ቦታዎች ጥቃት ሲያርሱ እንደነበር  ገልጸው፤ አሁንም የአካባቢው ጸጥታ ኹኔታ  አሳሳቢ መሆኑንን ነዋሪዎች አብራርተዋል፡፡

የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽ ጉዳዩች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ በበኩላቸው ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸማቸውንና በሰው ሕይወት ላይም ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል፡፡ ያምፒ በተባለች እና ሌሎች ቀበሌዎች ሰሞኑን በነበረው ጥቃት  ምክንያት ከ1800 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት ዐስታውቋል፡፡ የኢትዩጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የጸጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ባለፈው እሁድ ባወጣው መግለጫ «የፌዴራልና የክልሉ የፀጥታና የፍትሕ አካላት ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመሆን እነዚህን ጥቃቶች ሊያስቆም የሚችል አዲስ ክልላዊ የፀጥታ ስትራቴጂ ሊነድፉ ይገባል» ብለዋል፡፡

ትናንት ከሰዓት በድባጢ ወረዳ ሶስት በሚደርሱ ቀበሌዎችም ውስጥ ታጣቂዎች በመንቀሳቀስ ጥቃት ማድረሳቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ አቶ ባይሳ ማሞ በድባጢ ወረዳ የጋለሳ  ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በጋለሳ እና አጎራባች ከሆኔው  ሙዛን እና ቆርቃ በተባሉ የድባጢ ወረዳ ቀበሌዎች  ታጣቂዎች ትናንት  ባደረሱት ጥቃት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ለዲዳቢሊው ገልጸዋል፡፡  500 የሚደርሱ ነዋሪዎችም መፈናቀላቸውንም ተናግዋል፡፡ ጥቃት አድራቹም የሚታወቁና ከተለያዩ ቀበሌዎች ተሰባስበው ጉዳት ማድረሳቸውን  የአካባቢ ነዋሪዎች  አብራርተዋል፡፡

ከድባጢ ወረዳ ከተማ በ7 ኪሜ ርቀት ላይ በሚገትገኝዋ ያምፒ ቀበሌ ነዋሪ የሑኑት አቶ ምትኩ ላሚ ባለፈው ቅዳሜ በያምፒ ቀበሌ በነበረው  የታጣቂዎች ጥቃት ምክያንት ተፈናቅለው በድባጢ ወረዳ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በወረዳው እሳቸውን ጨምሮ 789  የአካቢው ነዋሪዎች ተፈናቅለው ባአንድ ስፋራ እንደሚገኑ አመልክተዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ በያምፒ በነበረው ጥቃት አንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ  የፖሊስ አባላት መቆሰለቻውን አክለዋል፡፡

የመተከል ዞን  የጸጥታ ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራን ነው ያሉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ታጣቂዎች በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸዋል፡፡ የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ በበኩላቸው የተፈናቃዩች ቁጥር እየጨመረ መሆኑንን ተናግረዋል፡፡ በድባጢ ወረዳ በተለያዩ ቀበለዎች በዚህ ሳምንት በነበረው ተደጋጋሚ ጥቃቶች በርካታ  ዜጎች ወደ ድባጢ ከተማ  ሸሽተው በመጠለያ ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ 

የክልሉ መንግሰት 20 ጸረሰላም ያላቸው ሀይሎች   ላይ እርምጃ መውዱንም ትናንት አስታውቆ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ህዳር ስድስት ባወጣው መግለጫው “በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ፋታ የማይሰጥ ሆኖ በመቀጠሉ፤ በፌዴራልና በክልሉ መንግሥታት የፀጥታ ኃይሎች መካከል በፍጥነትና ንቁ ሆኖ መጠበቅ ላይ የተመሰረተ የተሻለ ቅንጅት የሚሻ ነው። ሲል ኮሚሽኑ በመግለጫው አብራርተዋል፡፡

ነጋሣ ደሳለኝ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic