1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቄለምና ምዕራብ ወለጋ የተወሰኑ ስፍራዎች የኢንተርኔት እና ስልክ መቋረጥ

ሐሙስ፣ ኅዳር 17 2013

በቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ዞን የተወሰኑ ስፍራዎች የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ከጠፋ ከሁለት ሳምንት በላይ ሆኖታል። ከአካባቢው ወደ ጊምቢ እና ነቀምቴ ከተማ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎችና ዘመዶቻቸውን ከስፍራው መጠየቅ አለመቻላቸውን የነገሩን የግምቢ እና ነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ስለ አገልግቱ መቋረጥ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3ls11
Äthiopien Addis Abeba | Ethio Telecom building
ምስል DW/H. Melesse

በቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ የተወሰኑ ስፍራዎች የኢንተርኔት እና ስልክ መቋረጥ

በቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ዞን የተወሰኑ ስፍራዎች የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ከጠፋ ከሁለት ሳምንት በላይ ሆኖታል። ከአካባቢው ወደ ጊምቢ እና ነቀምቴ ከተማ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎችና ዘመዶቻቸውን ከስፍራው መጠየቅ አለመቻላቸውን የነገሩን የግምቢ እና ነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ስለ አገልግቱ መቋረጥ ተናግረዋል። አገልሎቱ የተቋረጠበትን ምክንያት እስካሁን በመንግስት አካል አልተገለጸም። 
የምዕራብ ወለጋ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ ኡመታ በዞናቸው ስር  ስምንት በሚደርሱ ወረዳዎች የሞባይል ስልክ አገልግሎት መቋረጡን እና ችግሩን ለመቅረፍ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እየተነጋሩ እንደሆነ ተናግረዋል። በምዕራብ ወለጋ ጊምብ ከተማ ነዋሪ እና በማሽከርከርና ስራ የተሰማሩ አቶ ቡልቱም በዞኑ የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት ከጥቅምት ወር መጨረሻ አንስቶ መጥፋቱን ገልጸዋል። የኔትወርኩ መቋረጥ ምክንያት እስካሁን አለመታወቁን እና በመቻራና ሳዩ ከተባሉ ስፍራዎች ከዘመዶቻቸው ጋር መገናኘት እንዳልቻሉ አክለዋል። በጉሊሶ ጥቃት ከደረሰ ወዲህ በአካባቢው በስልክ እና በኢንተርኔት አገልግት መጥፋቱን አብራርተዋል።
በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አቶ ጅባቲም እንደዚሁም በግዳሚ እና ነጆ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ባለመኖሩ ከዘመዶቻቸው ጋር መገናኘት እንዳቻሉ ተናግረዋል።  በነቀምቴ  ኢትዮ ቴሌኮም ቢሮ መረጃ ቢጠይቁም የጠፋበትን ምክንያት ለማወቅ አልተቻለም ብለዋል።  
የምዕራብ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ ሁመታ በዞናቸው ስር በሚገገኙ የወረዳዎች የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ስለመቋረጥ ገልጸው የተቋረጠበትን ምክንያት ግን እንደማያውቁ ጠቁመዋል።
የአገልግሎት መቋረጥ አስመልክቶ የጠየቅናቸው የኦሮሚያ ክልል ኮምዩንኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ስለመቋረጡ ምክንያት እንደማያውቁ ገልጸው በጸጥታ ችግርም ሆነ በሌላ ምክንያት የቴሌኮም አገልግሎት እንዲቋረጥ የተላለፈ ውሳኔም በመንግስት በኩል የለም ብለዋል። 
በነቀምቴ ከተማ የሚገኙ የምዕራብ ሪጅን ኢትዮ ተሌኮም ቢሮ እና ከኢትዮ ቴለኮም ዋና ቢሮ ስለጉዳዩ መረጃ ለማግኘት በስልክ ያደረኩት ጥረት አልተሳካም። 
ባለፈው ዓመትም  ከታህሳስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት ያህል በወለጋ ዞኖችና በተወሰኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወረዳዎችም  የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ የክልሉ መንግስት የአካባቢውን የጸጥታ ችግርን ለመቅረፍ ሲባል መቋርጦ ገልጾ ነበር።

ነጋሳ ደሳለኝ

እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ