በቀድሞ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ኃላፊና ሠራተኞች ላይ የቀረበው ክስ | ኢትዮጵያ | DW | 08.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በቀድሞ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ኃላፊና ሠራተኞች ላይ የቀረበው ክስ

የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር እንደገለፀው በተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበው ክስ ተመሳሳይነት አለው። ችሎቱ አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ አራት ተጠርጣሪዎች የፌደራል ፖሊስ ባሉበት መጥሪያ እንዲሰጣቸው አቃቤ ሕግ በጠየቀው መሠረት ነገ ለፖሊስ ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:18

አቃቤ ህግ በቀድሞ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ኃላፊና ሠራተኞች ላይ የቀረበው ክስ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ልደታ ምድብ፤ አንደኛ ችሎት በቀድሞ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ኃላፊና ሠራተኞች ላይ የቀረበውን ክስ ዛሬም ማድመጡን  ቀጥሏል። በዛሬው ችሎት የአንደኛውን ተከሳሽ የአቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ ከ5 ተኛ እስከ 19ኛ የተዘረዘሩ ተካሶችን ክስ አዳምጧል። ችሎቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር በተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበው ክስ ተመሳሳይነት እንዳለው ተናግሯል። ችሎቱ አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ አራት ተጠርጣሪዎች የፌደራል ፖሊስ ባሉበት መጥሪያ እንዲሰጣቸው አቃቤ ሕግ በጠየቀው መሠረት ነገ ችሎት ያልቀረቡትን ተከሳሾች በተመለከተ ለፖሊስ ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ስለ ዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት ዬሐንስን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ዮሐስ ገብረ እግዚአብሔር 

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ
 

Audios and videos on the topic