1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሴኔጋል ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ፉዬ አሸነፉ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 17 2016

በሴኔጋል ባለፈው ዕሁድ በተደረገው ፕረዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ ሚስተር ባሲሮ ዲዮማየ ፋየ አሸናፊ መሆናቸው ተገልጿል። ምንም እንኳ ውጤቱ በይፋ የሚገለጸው በሚቀጥለው አርብ ቢሆንም፤ ብዙዎቹ ተፎካካሪዎች ከግዚያዊ ውጠቱ በመነሳት የሚስተር ፋየን አሸናፊነት መቀበላቸውን አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/4e92b
Senegals gewählter Präsident Bassirou Diomaye Faye
ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ አዲሱ የሴኔጋል ፕሬዚዳንትምስል Luc Gnago/REUTERS

ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ አዲሱ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

የተጠበቀው የሴኔጋል ምርጫ

በሴኔጋል ባለፈው ዕሁድ በተደረገው ፕረዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ  ሚስተር ባሲሮ ዲዮማየ ፋየ አሸናፊ መሆናቸው ተገልጿል። ምንም እንኳ ውጤቱ  በይፋ የሚገለጸው በሚቀጥለው አርብ ቢሆንም፤ ብዙዎቹ ተፎካካሪዎች ከግዚያዊ ውጤቱ በመነሳት የሚስተር ፋየን አሸናፊነት የተቀበሉ በመሆኑና የገዥው ፓርቲ እጩ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስተር አማዶ ባየም ማሸነፋቸውን በማመን በመጀመሪያ ዙር ውድድር አሸናፊ ለሆኑት ሚስተር  ዲዮማየ  ፋየ  የደስታ መልክት በማስተላለፋቸው፤ የምርጫው ውጤት እንዳለቀለትና እንደታወቀ ተወስዷል።

የምርጫው ዉጤትና የአሸናፊው ፕሪዝደንት መልዕክት

ከሴነጋል 7 ሚሊዮን መራጭ ህዝብ የገዥው ፓርቲ እጩ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስተር ባ 36.2 ከመቶ ድምጽ ሲያገኙ፤ ሚስተር ዲዮማየ 53.7 ድምጽ በማገኘት ያለ ሁለተኛ ዙር ውድድር አሸናፊ ሁነዋል።፡ሚስተር ዲዮማየ ተፎካካሪዎቻቸው አሸናፊነታቸውን እውቅና ከሰጡት በኋላ ባደረጉት ንግንግግር፤ አገራቸውን በታማኘት ለማገልገል ቃል ገበተዋል፤ “ አገሬን በታማኝነትና ግልጽነት ለማገልገል እጥራለሁ፤ በየትኛውም ደረጃ ያለውን ሙስናም እዋጋለሁ፤ ተቋምቶቻችንንም እንደገና እገነባለሁ” በማለት አሸናፊነታቸውን ቀድመው ዕውቅና ለሰጡ ተፎካካሪዎችና ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ጭምር ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል።ለአፍሪካ በዴሞክራሲ በምሳሌነት ትቀጠስ የነበረችው ሴኔጋል ምን ገጠማት?

የሴኔጋል የምርጫ ኮሚሽን
ከሴነጋል 7 ሚሊዮን መራጭ ህዝብ የገዥው ፓርቲ እጩ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስተር ባ 36.2 ከመቶ ድምጽ ሲያገኙ፤ ሚስተር ዲዮማየ 53.7 ድምጽ በማገኘት ያለ ሁለተኛ ዙር ውድድር አሸናፊ ሁነዋል።ምስል Luc Gnago/REUTERS

በሴኔጋል የታየው ቅድመ ምርጫ ቀውስ

ሴናጋል በተረጋጋ መንግስታዊ ስራቷና ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎቿ በምዕራብ አፍሪካ ተጠቃሽ አገር ብትሆንም፤  ካለፉት ጥቂት አመታ ወዲህ ግን አመጽ የታክለበት ተቃውሞን ስታስተናግድ የቆየች በመሆኗ፤ ይህ ምርጫ በብዙዎች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ እንደነበር ነው የሚነገረው።  ባለፈው የካቲት ወር ሊደረግ የሚገባው ምርጫ መተላለፉና ፕሬዝዳንት ሳል ከህገመንግስቱ ውጭ ለሶስተኛ ግዜ ሊወዳደሩ ነው መባሉ፤ እንዲሁም አሁን አሸናፊ የሆኑትና ሌላው  የተቃዋሚ መሪ ሚስተር  ሶንኮ በመታሰራቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቶ፤ ሰዎች እንደሞቱና አንድ ሺ ያህል ደግሞ እንደታሰሩ የመብት ድርጅቶች ይፋ አድርገው ነበር። ሚስተር ዲዮማየ ለዚህ በመጀመሪያ ዙር አሸናፊ በሆኑበት ምርጫ የተወዳደሩትም፤  ከአስር ቀን በፊት ከእስር ቤት ወተው እንደሆነ ታውቋል። ከሳቸው ጋር ታስረው የነበሩትና የተፈቱት ሌላው ታዋቂ ተቃዋሚ ሚስተር ሶንኮ ግን ባለባቸው የፍርድ እግድ ምክኒያት ለውድድር ሊቀርቡ ባለመቻላቸው ድጋፋቸውን ለሚስተር ዲዮማየ በመስጠትና አብረዋቸውም በምርጫ ዘመቻው በመሳተፍ ለሚስተር ዲዮማየ ማሸነፍ ትልቅ ሚና እንደተጫወቱ ነው የሚነገረው።ማኪ ሳል ለሦስተኛ ዘመነ ስልጣን አልወዳደርም አሉ

የምርጫው ሰላማዊነትና ታሪካዊነት

ምርጫው ሰላማዊና ምንም አይነት ችግር ያልተስተዋለበት ከመሆኑም በላይ በሂደቱና ውጤቱ  ተቃዋሚ ተወዳሪዎችን ሳይቀር ያስደስተና ያረካ እንደሆነም እየተነገረ ነው። ሚስተር ክሪስቶፈር ኦጉንሞዴድ የተባሉ ሴኔጋላዊ የፖለቲካ ተንታኛ፤ ምርጫው ታሪካዊና ወሳኝ የሆነበትን ምክኒያት ሲገልጹ፤ “ አንደኛ ምርጫው ለመጅመሪያ ጊዜ  በስልጣን ላይ ያለ  ፕሬዝዳንት ያልተወዳደረበት መሆኑ ነው።

አህመዱ ባ የተጣማሪ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪ
ምርጫው ሰላማዊና ምንም አይነት ችግር ያልተስተዋለበት ከመሆኑም በላይ በሂደቱና ውጤቱ  ተቃዋሚ ተወዳሪዎችን ሳይቀር ያስደስተና ያረካ እንደሆነም እየተነገረ ነው።ምስል Luc Gnago/REUTERS

ከሁሉም በላይ ግን ተፍጥሮ የነበረው የፖለቲካ ቀውስ አልፎ የተደረገ በመሆኑና ሲኔጋልም በአስቸጋሪ የኢኮኖሚ ሁኒታ ባለችበትኔ ወቅት የተካሄደ በመሆኑ ታሪካዊና ወሳኝ ያደርገዋል ብለዋል።የሴኔጋል ተቃውሞ የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት ይጎዳ ይሆን?

የአዲሱ ፕሬዝደንት ማንነትና ትኩረታቸው

የ44 አመቱ አሽናፊ ፕሬዝዳንት ሚስተር ዲባሲሮ ዲዮማየ ፋየ በሴንጋል ፖለቲካ ከዚህ ቀደም ብዙም የማይታወቁ፤ ግን ከነበሩት ተፎካካሪዎች ተራማጅና የለውጥ አራማጅ መሆናቸው የሚነገርላቸው መሆኑን  የፍራንስ 24 ጋዜጠኛ   ሳም ብራድፒስ ከዳካር ሲናገር ተሰምቷል፤ “ በዚህ ውድድር ከቀረቡት ሁሉም ተፎካካሪዎች ተራማጅና ሲኔጋልን የቅኝ ግዛት ውርስ ከሆነው የሴፋ የመገበያያ ገንዘብ  ማስወጣት የሚሹ ናቸው” በማለት በርካታ የለውጥ ሀሳቦች እንዳሏቸው የሚነገር መሆኑን አውስቷል

 ምርጫውን የምራብ አፍርካ የኢኮኖሚ ትብብር- ኢክዋስና የሴንጋል የሲቪል ማህበራት ጥምረት እንደተዛቡት የታውቀ ሲሆን፤ በምርጫው ሂደት የጎላ ችግር የነበረ ስለመሆኑ እስካሁን አልተገለጸም።  ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል እ እ እ አቆጣጠር ሚያዚያ ሁለት ከስልጣንን የሚወርዱ ሲሆን ዛሬ ከምራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር -  ኢኮዋስ፤ የአውሮፓና የአፍርካ ህብረት ተወክዮች ጋር በዝግ ተሰብስበው ስለምርጫውና የሽግግር ሂደቱ እንደተወያዩ ታውቋል።

ገበያው ንጉሴ

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ