በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ባለፈው ዓርብ በደረሰ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ። በወረዳው በመረዳዳት እና ተሳስበው በሚኖሩ ሁለት ብሔሮች መካከል ልዩነት ለመፍጠር በተንቀሳቀሱ አካላት ተከስቷል በተባለው በዚህ ግጭት በተለያዩ የዕድሜ ክልሎች የሚገኙ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው ተገልጿል።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ባለፈው ዓርብ በደረሰ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ተናገሩ። በወረዳው በመረዳዳት እና ተሳስበው በሚኖሩ ሁለት ብሔሮች መካከል ልዩነት ለመፍጠር በተንቀሳቀሱ አካላት ተከስቷል በተባለው በዚህ ግጭት በተለያዩ የዕድሜ ክልሎች የሚገኙ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በጥቃቱ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ እና በአከባቢው ይኖሩ የነበሩ የአማራ እና የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች በተለይም ጥቃቱ ከተፈጸመበት መቱ ስላሴ ቀበሌ ቀዬያቸውን ጥለው መሰደዳቸውን ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል። ግጭቱ የብሔር ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው አካላት እንደፈጸሙት የዞኑ አስተዳዳሪ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ። የጸጥታ ኃይሎች በአከባቢው ተሰማርተው ማረጋጋታቸውንም አስረድተዋል።
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሰ