1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በምርጫ እንድሳተፍ የሚፈቅድ አውድ የለም - ኦፌኮ 

ሰኞ፣ የካቲት 15 2013

በዓመቱ ማገባደጃ ለሚደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ የእጩዎች ምዝገባ ቀነ ገደብ ከሳምንት ያነሰ ጊዜ ቢቀረውም እስካሁን አንድም እጩ ተወዳዳሪ አለማስመዝገቡን የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦ.ፌ.ኮ) አስታወቀ፡፡

https://p.dw.com/p/3piPW
Äthiopien Oromo Federalist Congress
ምስል Seyoum Getu/DW

ኦፌኮ እስካሁን አንድም እጩ ተወዳዳሪ አላስመዘገበም

በዓመቱ ማገባደጃ ለሚደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ የእጩዎች ምዝገባ ቀነ ገደብ ከሳምንት ያነሰ ጊዜ ቢቀረውም እስካሁን አንድም እጩ ተወዳዳሪ አለማስመዝገቡን የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦ.ፌ.ኮ) አስታወቀ፡፡ 
የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት በፓርቲው አባላትና አስተባባሪዎች ላይ የሚደረግ እስራት አሁንም አልተቋጨም፡፡ 
በየአከባቢው የሚገኙ ጽሕፈት ቤቶችም በከፊል ሲዘጉ ክፍት በሆኑትም በተረጋጋ መልኩ የምርጫ ቅስቀሳ እና ሌሎች ተግባራትን መተግበር አለመቻሉንም ፓርቲው አክሎ ገልጧል፡፡  ገዢው ብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ ምርጫውን ሰላማዊና ነጻ አውድ የሚስተዋልበት እንዲሆን ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ 
ስዩም ጌቱ 

አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ