በማድመጥ መማር | በማ ድመጥ መማር | DW | 15.01.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

በማ ድመጥ መማር

በማድመጥ መማር

ትምህርት ለአፍሪቃ እድገት ቁልፍ ሚና አለው። ይሁንና ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች በበቂ ሁኔታ የሉም። በማዳመጥ መማር የተባለው የዶቼ ቬለ አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን የርቀት ትምህርት በሁሉም የአህጉሪቱ ክፍሎች እውቀትን ለማዳረስ ይጥራል።

default

በማድመጥ መማር

በአሁኑ ወቅት በአፍሪቃ ው ጤ ታማ ለመ ሆን የሚ ያስፈልጉ ክሎች

ትምህርት ለአፍሪቃ እድገት ቁልፍ ሚና አለው። ይሁንና ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች በበቂ ሁኔታ የሉም። በማዳመጥ መማር የተባለው የዶቼ ቬለ አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን የርቀት ትምህርት በሁሉም የአህጉሪቱ ክፍሎች እውቀትን ለማዳረስ ይጥራል።

አፍሪቃ ውስጥ ነገሮች በፍጥነት እየተለወጡ ነዉ። ተንቀሳቃሽ ስልኮችና ኢንተርኔት በከፍተኛ ደረጃ በመስፋፋት ላይ ቢሆኑም በሺዎች የሚ ቆጠሩ ሰዎች የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ዎች አይደሉም። ወጣት አፍሪቃውያን በዓለም አቀፍ የአፅናፋዊ የምጣኔ ሃብት ትስስር (ግሎባላይዜሽን) ዘመን በምን ዓይነት መልኩ የዚህ ተጠቃሚዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ያስባሉ። ወደ ተሻለ የሥራና የትምህርት እድል የሚወስዳቸውን መንገድም ያስሳሉ። ለምሳሌ፤ ምን ዓይነት ትምህርትና ሥራ በመረጃ መረብ አማካኝነት ከርቀት ማግኘት ይችላሉ? እንደሚ ታወቀው ብዙ ወጣት አፍሪቃውያን ለትምህርት ወደ አውሮጳ መሄድ ቢፈልጉም እዛ ምን እንደሚጠብቃቸው አያውቁም።

ማስተማሪያ

ዶቼ ቬለ ለውጥ ማምጣት ይፈልጋል። አድማጮች ቀደም ሲል የተገለፁትን ችግሮች እንዴት መፍታት እንዳለባቸው አዝናኝና አስተማሪ በሆነ መንገድ ያስተምራቸዋል። በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት እያዝናኑ የሚ ያስተምሩ የሬድዮ ጭውውቶች በማቅረብ አድማጮች በአዲሲቷ አፍሪቃ ውጤ ታማ ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን ክሂል እንዲጨብጡ ያግዛቸዋል።

ተሳትፎ

ዝግጅቶቹ በዶቼ ቬለ ራድዬ ሰራተኞች በመታገዝ በአፍሪቃውያን ጸሐፊዎች ይዘጋጃሉ። በአማርኛ፣ ሃውሳ፣ ኪስዋሂሊ፣ እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛና ፓርቱጋልኛ፤ በአጭር ሞገድና በሳተላይት ይሰራጫሉ። ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ አጋር ጣቢያዎችም የበማዳመጥ መማር ዝግጅትን እንደገና ተቀብለው በመላው አፍሪቃ ያሰራጫ ሉ።

በተጨማሪም ሁሉንም ዝግጅቶች ለመከታተል

www.dw-world.de/lbe የተሰኘው ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ፕሮጀክት በጀርመን ፌደራላዊ የውጪ ጉዳይ ሚ ኒስቴር ይታገዛል።