1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በመቐለ በቀን 270 ምርመራዎች ማድረግ የሚችል ላብራቶሪ ስራ ጀመረ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 26 2012

ቻይና ለአፍሪካ በለገሰቻቸው ቁሳቁሶች በመቐለ ከተማ በቀን 270 ምርመራዎች ማድረግ የሚችል ላብራቶሪ ስራ ጀመረ። የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ተወልደ ውብአየሁ በላብራቶሪው የሚገኘው ማሽን በአንድ ጊዜ 90 ምርመራዎች ማድረግ እንደሚችል ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3aSZE
Coronavirus in China Changzhou Testlabor
ምስል፦ AFP

የኮሮና ምርመራ በትግራይ ተጀመረ

በቀን 270 የኮረና ቫይረስ ተጠርጣሪዎችን የመመርመር አቅም ያለው የኮረና ቫይረስ ላብራቶሪ በመቐለ ስራ ጀመረ፡፡ የኮረና ቫይረስ ምርመራ ማእከል በኢትዮጵያ ክልል ከተማ ሲደራጅ የመቐለው የመጀመሪያ ነው፡

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል የኮረና መድሃኒት አለን ብለው ወሬ ያሰራጩ 'የባህል መድሃኒት አዋቂዎች' በተባሉ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ የትግራይ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

እሸቴ በቀለ