በመቀሌ የእግር ኳስ ጨዋታ የተፈጠረው ግጭት | ኢትዮጵያ | DW | 14.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በመቀሌ የእግር ኳስ ጨዋታ የተፈጠረው ግጭት

ትናንት በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ስቴዲዮም በነበረ የእግር ኳስ ግጥሚያ ግጭት መፈጠሩ ተሰምቷል ። የእግር ኳስ ጨዋታው የመቀሌ ከነማ እና የባህርዳር ከነማ በብሔራዊ ሊግ የሚያካሂዱት መደበኛ ግጥሚያ ነበር።

ግጭቱ የተቀሰቀሰው ግጥሚያው በመካሄድ ላይ እያለ እንደነበር የአይን እማኞች ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል። ግጭቱን ለማስቆም ጣልቃ የገባው ፖሊስ አስለቃሽ ጪስ መተኮሱን እና ተመልካቾች መደብደባቸውን የዓይን እማኞቹ ይናገራሉ። በዚህም መሠረት ጨዋታው ሳይጠናቀቅ ታዳሚው ተበትኗል። ያነጋገርናቸው ሁለት የዓይን እማኞች የገለፁልንን ከዚህ በታች ተጭነው ሊያዳምጡ ይችላሉ። በጉዳዮ ላይ የትግራይ ክልል ፖሊስን እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም።

ልደት አበበ

ተስፋለም ወልደየስ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች