በሆሮ ጉዱሩ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች በንጹሃን ላይ ያነጣጠረ ግድያ | ኢትዮጵያ | DW | 16.12.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በሆሮ ጉዱሩ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች በንጹሃን ላይ ያነጣጠረ ግድያ

የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ዛሬ ለብዙሃን መገናኛ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ከትናንት በስቲያ እና ለሊት ለትናንት አጥቢያ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በ13 የአማራ ተወላጆች፤ በምዕራብ ወለጋ ነጆ ወረዳ ደግሞ በ6 የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የጅምላ ግድያ "ኦነግ ሸነ" ባሉት ታጣቂ ቡድን ግድያ ተፈጽሟል። 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:12

በሆሮ ጉዱሩ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች በንጹሃን ላይ ያነጣጠረ ግድያ

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሁለት ቀናት ቢያንስ በሁለት ዞኖች ብቻ 19 ንፁሃን ዜጎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የክልሉ መንግስት አረጋገጠ።  የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ዛሬ ለብዙሃን መገናኛ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ከትናንት በስቲያ እና ለሊት ለትናንት አጥቢያ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በ13 የአማራ ተወላጆች፤ በምዕራብ ወለጋ ነጆ ወረዳ ደግሞ በ6 የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የጅምላ ግድያ "ኦነግ ሸነ" ባሉት ታጣቂ ቡድን ተፈጽሟል። ኃላፊው አክለውም በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ከተፈጸመው ጥቃት ወዲህ በክልሉ "ህግን ለማስከበር ተወስዷል" ባሉት እርምጃ በርካታ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ 782 የሸማቂ ቡድኑ አባላት ላይ እርምጃ ተወስዷል ነው ያሉት። 
በሌላ በኩል ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ተብለው የተጠረጠሩ 808 የመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚሰሩ አመራሮችና የጸጥታ ዘርፉ አባላት ላይም ከኃላፊነት የማንሳት እና ለህግ የማቅረብ እርምጃ ተከናውኗል ነው የተባለው።

ስዩም ጌቱ

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ
 

Audios and videos on the topic