1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቄሌም ወለጋ በፀጥታ ችግር የሰዎች ሕይወት እየጠፋ ነው

ረቡዕ፣ መጋቢት 4 2016

በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ እና በምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ ውስጥ በሚስተዋለው የፀጥታ ችግር በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን የአካባቢው ነዋሪዎኢትዮጵያች አስታወቁ ። አልፎ አልፎ በታጣቂዎች እና ጸጥታ ኃይላት መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ አሁንም ጉዳት እየደረሰ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4dT6d
Äthiopien Qelem welega
ምስል Negassa Dessalegn/DW

አንድ ሰላማዊ ሰው በፀጥታ ኃይላት ሕይወቱ ማለፉ ተገልጧል

በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ እና በምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ ውስጥ በሚስተዋለው የፀጥታ ችግር በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ ። አልፎ አልፎ በታጣቂዎች እና ጸጥታ ኃይላት መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ አሁንም ጉዳት እየደረሰ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በተለይም አርሶ አደሩ በሚፈልገው መልኩ ወደ ገበያ ሄዶ ምርቱን መሸጥና መነገድ አዳጋች እየሆነበት እንደሚገኝ ገልጠዋል ። ከትናንት በስቲያ በቆንዳላ ወረዳ አንድ ሰላማዊ ሰው በፀጥታ ኃይላት ሕይወቱ ማለፉ ተገልጧል ። የወረዳው አስተዳደር በበኩሉ በፀጥታ ኃይላት የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አመልክተዋል።

የቄለም ወለጋ ዞን ለረጅም ጊዜ የቆየ የጸጥታ አለረመጋጋት ከተስተዋለባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከዞኑ ጊዳሚ ወረዳ አስተያየታቸውን የሰጡን አንድ ነዋሪ በአካባቢው አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶች በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት ከማድረስ በተጨማሪ የነዋሪውን እንቅስቃሴ መገደቡን አመልክተዋል፡፡ በአካባቢአቸው ያለው የፀጥታ ችግር ትኩረት እንዳልተሰጠው ይናገራሉ፡፡

በፀጥታ ችግር ሳቢያ አሁንም በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው

«አርሶ አደሩ ገበያ ሄደው መመለስ አልቻለም፡፡ ያለውን ምርት ገበያ ወስደው መሸጥ አልተቻለም፣ ዝርፍና የተለያዩ ጉዳች ሊደርስበት ይችላል፡፡ ከፍተኛ ችግር ነው በዚህ አካባቢ ያለው፡፡ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ያሉ አለመግባባቶችን በሽምግልና እና ዕርቅ ቢፈቱ አርሶ አደሩ ያለ ስጋት መኖር ይችላል፡፡»

በሠላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም

ከምዕራብ ወለጋ  ዞን ቆንዳላ ወረዳ አስተያየተቸውን የሰጡን ሌላው ነዋሪም ሸማቂዎችና የመንግስት ፀጥታ ሐይሎች መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ሰላማዊ ሰዎች እየተጎዱ እንዲሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ ሰኞ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ 27፣ መጋቢት 2016 ዓ.ም ደግሞ ዳንካረ በሚባል ቦታ አራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸዋል፡፡

«ሁለቱ ኃይሎች በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሰላምዊ ሰዎች እየተጉዱ ነው፡፡ የትራንስፖርት ችግርም አለ በፀጥታ ችግር ምክንያት በኢኮኖሚምና በጤናም ኅብረተሰቡ ተጎድቷል፡፡ አካባቢው በግብርናም በንግድም የታወቀ ነው፡፡ ኅብረተሰቡ ያመረተውን ወደ ገበያ ወስዶ እየሸጠ አይደለም፡፡»

የቆንዳላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዳንኤል ደሳለኝ በሰጡን ምላሽ በወረዳቸው በፀጥታ ኃይሎች ሕይወቱ ያለፈ ሰላማዊ ሰው አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው ይንቀሰቀሳሉ ያሉት ጠላት ብለው የጠሯቸው ኃይሎች መንገድ በመዝጋት ሰዎች እንዳይነግዱና አርሶ አደሩ ምርታቸውን ወደ ገበያ እንዳይወስዱ ያደርጋሉ ብሏል፡፡

በፀጥታ ችግር ምክንያት በኢኮኖሚምና በጤናም ኅብረተሰቡ ተጎድቷል፡፡
በአካባቢው በፀጥታ ችግር ምክንያት በኢኮኖሚምና በጤናም ኅብረተሰቡ ተጎድቷል፡፡ ምስል Negassa Dessalegen/DW

በአካባቢው ግጭቶች በየጊዜው ይከሰታሉ

«ግጭቶች አልፎ አልፎ ይኖራሉ ነገር ግን አንድም ሰላማዊ ሰው አልሞተም፡፡ ታጥቆ በሚንቀሳቀስ ጠላት ጋር በሚደረገው ፍልያ እርምጃዎች ይወሰዳሉ፡፡ ሰላማዊ ሰዎችን እየገደለ ያለው ጠላት ነው፡፡ ገበያ እንዳትሄዱ ተብሎ ይታወጅል፡፡ ገበያ የሚሄድ ሞተርና መኪና ይቃጠላል፡፡ ገንዘብ መንጠቅ መዝረፍ ያለ ነው፡፡ ይሄን የሚያደርገው ጠላት ነው፡፡»

በጊዳሚ ወረዳ የተነሳውን የነዋሪዎች የፀጥታ ስጋትን አስመልክቶ ከቄሌም ወለጋ ዞን ዋና አስተዳደር ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን በስልክ ያደረኩት ጥረት ስልላካቸውን ባለማንሳታቸው አልተሳካም፡፡ በምዕራብ ኦሮሚያ ያለውን የሰላም እጦት አስልመክቶ በመንግስትና ሸማቂዎች እርስ በዕረሳቸው ሲወቃቀሱ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ የሚታየውን የሰላም ችግር ለመፍታት መንግስትና የኦሮሞ ነጻነት ስራዊት መካከል ተጀምሮ የነበረው ድርድር አሁንም እንዲቀጥር ነዋሪዎች ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ነጋሣ ደሳለኝ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ዮሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር