ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
እርስ በርስ ጦርነት፣ ሙስና እና ድርቅ የምስራቅ አፍሪቃዊቱን ሐገር ቀዉስ ዉስጥ ከተዋታል።
እ.ጎ.አ. በ1991 የረዥም ጊዜ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት የነበሩት ዚያድ ባሬ ከስልጣን ተወገዱ ።በተቃዋሚ ኃይላት መካከል ለ30 ዓመታት አመታት የዘለቀው ጦርነት ሐገሪቱን አዉድሟታል።ሶማሊያ እንደ አልሸባብ ያሉ የአሸባሪ ቡድኖች ተፅዕኖ የሚፈጥሩባትም ሀገር ናት።
የድህነት በሽታ የሚባለው ኮሌራ በንጽሕና ጉድለት የሚከሰት እንደመሆኑ በተለይ የንጹሕ ውኃ አቅርቦት እና የመጸዳጃ አገልግሎት እጥረት የተንሰራፋባቸው ሃገራት ዋነኛ ችግር ነው። የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ከሰሞኑ በስምንት ዓመታት ውስጥ ኮሌራን የማጥፋት ዕቅድ እንደያዘ አመልክቷል።
በ2022 በርካታ ሕዝብ ከተገደለ፣ከሞተ፣ከተፈናቀለና ከተሰደደባቸዉ 20 ሐገራት አስራ አንዱ የአፍሪቃ ሐገራት ናቸዉ።ሶማሊያ፣ኢትዮጵያ፣ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ደቡብ ሱዳን፣ቡርኪና ፋሶ፣ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ፣ቻድ፣ማሊ፣ኒጀር፣ ናጄሪያ እና ሱዳን።
በጎርጎሪዮሳዊው የዘመን ቀመር 2028 ዓም የኬሌራ ወረርሽኝን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሉት ለስምንት ዓመታት በተያዘ እቅድ መሠረት ደግሞ በኮሌራ የሚከሰተውን የሞት ምጣኔ በ90 በመቶ ዝቅ ለማድርግ ተወጥኗል።
በሶማሌላንድ በእዚህ ዓመት ኅዳር ወር ላይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማካሄድ ነበረባት። መስከረም ወር ላይ ግን ከፍተኛ ተፅዕኖ ያለዉ የሽማግሌዎች ምክር ቤት፣ የፕሬዝዳንት ሙዝ ቢሂ አብዲን የስልጣን ዘመን ለሁለት ዓመታት አራዝሟል። በሚቀጥለው ዓመት ምርጫ ሊካሄድ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል፤ ይሁንና ስለመካሄድ አለመካሄዱ ገና በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም።
በአብዛኛዉ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ያሰለጠነና ያስታጠቀዉ ዳናብ ሰሞኑንም 100 የአሸባብ ተዋጊዎችን መግደሉን አስታዉቋል።ከአንድ መቶዉ ታጣቂዎች 60ዎቹ የተገደሉት ቡኩራ በተባለችዉ የደቡባዊ ሶማሊያ አነስተኛ ከተማና አካባቢ ነዉ
ሶማሊያ ውስጥ ድርቅ ያስከተለው የምግብ እጥረት የበርካቶችን ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል። ሱዳን ውስጥ ደግሞ ባለፉት ሳምንታት ዜጎች ለተቃውሞ አደባባይ በመውጣት ድምጻቸውን ማሰማታቸውን ቀጥለዋል።
ቅዳሜ ነዉ። መይሙናም ያወ-እንደ ወትሮዋ ልጆቿን ምሳ አብልታ ደግሞ ለእራት ተፍ-ተፍ ትላለች። ከቀኑ 8 ሰዓት።የመኪና ድምፅ፣ የልጆች ጫጫታ፣ የሽማች-ሻጭ፣የሸቃይ-አምታቺ ትርምስ የሚያካልበዉ ያ መንደር በአስደንጋጭ ድምፅ ተናወጠ።የምፅአት መለከት፣የሽብር ፊሽካ።ቦምብ ነዉ።
ኢትዮጵያ ለቻይናው ፖሊ ጂሲኤል ኩባንያ የሰጠቻቸውን የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ እና ልማት አምስት ፈቃዶች ሰርዛለች። ፖሊ ጂሲኤል እስከ ጅቡቲ 767 ኪሎ ሜትር ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ማጓጓዣ በ3.2 ቢሊዮን ዶላር ይገነባል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ኩባንያው ሥራውን ለማከናወን የፋይናንስና የቴክኒክ አቅም እንደሌለው የማዕድን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።