የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ
የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ
ለዋንጫ ግጥምያ የደረሱት የነዚህ ሁለቱ ሃገራት ተጋጣሚዎች ከፍተኛ ጨዋታን አሳይተዉ ኔዘርላንድ ፈረንሳይን ሁለት ለባዶ በመርታት የዋንጫዉ ባለቤት ሆናለች። በአዲስ አበባ ስቴድየም ለአንድ ቀን የተካሄደዉ የ2016 የአዉሮጳ እግር ኳስ ሻንፕዮና ጨዋታ ነፀ-ብራቅ ግጥምያ ጠንካራ ፉክክር የታየበት ነበር። ምርጥ የሴት እግር ኳስ ተጫዋች ከኔዘርላንድ፤ የወንድ ጠንካራ ተጫዋች ደግሞ ፈረንሳይን ወክለዉ ከተጫወቱ ወጣቶች ተመርጠዋል። በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ለኔዘርላንድ የተጫወተዉ ወጣት፤ ምርጥ በረኛ ደግሞ ኢጣልያን ወክሎ በግጥምያዉ ላይ የተሳተፈ ወጣት በመሆን ተመርጧል።
አዘጋጅ: ጌታቸዉ ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ/ አዜብ ታደሰ/ ሸዋዬ ለገሠ