ስጋቱ ያልቀነሰው የአተት ስርጭት
እሑድ፣ ግንቦት 20 2009ማስታወቂያ
በምስራቅ አፍሪቃ የኢትዮጵያ ጎረቤት በሆኑት ሶማልያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ ሰዎች ከጥቂት ጊዜ ወዲህ ተላላፊ ከሚባሉት በሽታዎች መካከል አንዱ በሆነው የኮሌራ በሽታ መያዛቸውን የመገናኛ ብዙኃን ዘገቦች አመልክተዋል። ብዙዎች በዚሁ በሽታ በመሰቃየት ላይ በሚገኙባት የመንም ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ መሆኑ እየተነገረ ነው። በኢትዮጵያ ደግሞ ካለፉት በርካታ ወራት ወዲህ በተለያዩ አካባቢዎች አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት በአህፅሮት «አተት» በሽታ ተከስቷል። በሽታው በተለይ በድርቅ በተመታው የሶማሌ ክልል አሳሳቢ መሆኑ ተሰምቷል። ተደጋግሞ የሚከሰተው የአተት ስርጭት ምክንያቶች ፣ የመከላከል ርምጃዎች፣ እንዲሁም ፣ ጎረቤት ሀገራትን ያሰጋው ኮሌራ እንዳይከሰት የሚደረገው ጥረት የተሰኙት ጉዳዮች የውይይታችን ትኩረት ናቸው።
አርያም ተክሌ
አዜብ ታደሰ