1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለድንበር ውዝግቡ የመቐለ ነዋሪዎች ምን አሉ?

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 10 2016

በተለይም ከቅርብ ቀናት ወዲህ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭቶች እያገረሹ ይገኛሉ። በዚህም ሞትና መፈናቀል ተከስቷል። የሁለቱ ክልል አስተዳደሮችም እርስ በራሳቸው እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/4ewM6
Äthiopien Hungersnot in Tigray
ምስል Million Hailesilassie/DW

ጦርነት አንገሽግሾናል፦ ነዋሪዎች

በተለይም ከቅርብ ቀናት ወዲህ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭቶች እያገረሹ ይገኛሉ። በዚህም ሞትና መፈናቀል ተከስቷል። የሁለቱ ክልል አስተዳደሮችም እርስ በራሳቸው እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ።

በግዛት ይገባኛል ጥያቄ የሚወዛገቡት  የትግራይ እና አማራ ክልሎች በተለይም በደቡብ ትግራይ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለሰዎች ሞትና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ ግጭቶች ከቅርብ ግዚያት ወዲህ እየተስተዋሉ ይገኛሉ።

የሁለቱ ክልሎች አስተዳደር አካላት በየፊናው የሚሰራጩ መግለጫዎች እንዲሁም መካረሮች ለዜጎችም አሳሳቢ ሆነዋል።

በመቐለ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች የሁለቱ ክልሎች መካረር እንዲበርድ፣ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲበጅ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ እና ሁሉም ችግሮች ከጦርነት መልስ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ ይጠይቃሉ።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሠ