ዲጂታል ዓለምአፍሪቃ
የዲጂታል ግንዛቤ «ሰው ሰራሽ እውነታ»ድራማ
ዓርብ፣ ሐምሌ 26 2016ማስታወቂያ
እምነት፣ ጀምበሬ እና ራሒም በደም ቢተሳሰሩም ስለ ህይወት እና ማህበረሰቡ ያላቸው አመለካከት የተለያየ ነው። እነሱም አስተያየታቸውን ከመናገር ወደ ኃላ አይሉም። አንዳንድ ጊዜም በዚህ አመለካከታቸው እርስ በርስ ይጣላሉ። ግን ደግሞ አንዳቸው ለሌላቸው ያስባሉ፣በችግር ጊዜም ይደርሳሉ። በደራሲ ጄምስ ሙሃንዶ የተፃፈው ይህ ታሪክ የኢንዙና ከተማ ሁለት የፖለቲካ እጩዎች ዝናቡ እና ቃቆ ለሚፎካከሩበት ምርጫ እንዴት እንደሚዘጋጁ ያስደምጠናል። ውጤቱ ይፋ በሚሆንበት ጊዜም የተለያዩ አስተያየቶችን ይሰጣሉ። ከተማ ውስጥም የሁለቱ ወገኖች ውጊያ የከፈቱበት ትርምስ ይከናወናል። ከዚህ ኋላ ያለው ሰው ማን ይሆን?
ደራሲ: ጀምስ ሙሀንዶ (ኬንያ)
ትርጉም : እሸቴ በቀለ
ፕሮዲውሰር : ልደት አበበ / ሃና ደምሴ