ራሳቸውን ከምርጫ ያገለሉ የድሪዳዋ እጩ ተወዳዳሪና ሐረሪ ክልል የሚንቀሳሱ ሌላ እጩ ተወዳዳሪ
ዓርብ፣ ግንቦት 14 2018
በ 7 ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከተሳተፉ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች በድሬደዋ - 1 ምርጫ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግል እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ሀብታሙ አለሙ (ዶ/ር) ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን ገለፁ ። ድሬደዋ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከምትወከልባቸው ሁለት ድምፃች በአንዱ ለመወዳደር ቀርበው ቅስቀሳ ሲያከናውኑ የነበሩት የግል እጩው ራሳቸውን ከምርጫው የማግለል ውሳኔ ላይ የደረሱት ላቀረቡት ቅሬታ "አጥጋቢ ምላሽ" ባለማግኘታቸው መሆኑን ጠቁመዋል።
ሌላኛው ለዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የሀረሪ ክልል ምክር ቤት የግል እጩ ተወዳዳሪው አቶ ጀማል አባገሮ እስካሁን ያለምንም እንከንየምረጡኝ ቅስቀሳ እያከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።
በ 7 ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከተሳተፉ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች በድሬደዋ - 1 ምርጫ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግል እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ሀብታሙ አለሙ (ዶ/ር) ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን ገለፁ ።
ድሬደዋ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከምትወከልባቸው ሁለት ድምፃች በአንዱ ለመወዳደር ቀርበው ቅስቀሳ ሲያከናውኑ የነበሩት የግል እጩው ራሳቸውን ከምርጫው የማግለል ውሳኔ ላይ የደረሱት ላቀረቡት ቅሬታ "አጥጋቢ ምላሽ" ባለማግኘታቸው መሆኑን ጠቁመዋል።
ሌላኛው ለዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የሀረሪ ክልል ምክር ቤት የግል እጩ ተወዳዳሪው አቶ ጀማል አባገሮ እስካሁን ያለምንም እንከን የምረጡኝ ቅስቀሳ እያከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።
ድሬደዋ ካሏት ሁለት የህዝብ ተወካዮች የውክልና መቀመጫዎች አንዱ በሆነው በድሬደዋ - 1 ምርጫ ክልል የግል እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ሀብታሙ አለሙ (ዶ/ር) "ለፍትህ አካላት እና ምርጫ ቦርድ ላቀረቡት አቤቱታ ተገቢ ምላሽ እንዳላገኙ በመጥቀስ" ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን ተናግረዋል ።
ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበር የጠቆሙት ዶክተር ሀብታሙ "የስም ማጥፋት ዘመቻ እና እንዲሁም በሀሰት የመወንጀል ዘመቻ ነበር" ብለዋል። ለሚመለከታቸው አካላት ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም አጥጋቢ ምላሽ አለማግኘታቸውን አስረድተዋል።
ዶክተር ሀብታሙ ላቀረቧቸው ቅሬታዎች ምላሽ ከመዘግየት ጋር በተገናኘ የምርጫ ቦርድን ወቅሰዋል። በሌላ በኩል ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው በሀረሪ ክልል ምክር ቤት የግል እጩ ተወዳዳሪው አቶ ጀማል አባገሮ "ያለምንም እክል" የምርጫ ቅስቀሳ እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። "የግል እጩ ተወዳዳሪ ሆነህ ስትቀርብ መዝነህ ነው" የሚሉት አቶ ጀማል ከሚፎካከሯቸው የገዢውም ሆነ ሌሎች የተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር እኩል ተፎካክረው ውጤታማ እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
7 ኛው ሀገራዊ ምርጫ እና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች እንቅስቃሴ
ዶይቼ ቬለ ለድምፅ መስጫው እለት የቀናት እድሜ ብቻ በቀረው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በግል እጩነት ከቀረቡት መካከል በድሬደዋ - 1 ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግል እጩ የሆኑትን ሀብታሙ አለሙ (ዶ/ር) እንዲሁም በሀረሪ ክልል ለክልሉ ምክር ቤት የግል እጩ ተወዳዳሪአቶ ጀማል አባገሮን በምርጫው የእስካሁን እንቅስቃሴያቸው ዙርያ አነጋግሯል።
በድሬደዋ -1 ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግል እጩ ሆነው የቀረቡት ዶክተር ሀብታሙ ፖስተሮችን በመለጠፍ እና በመኪና ላይ ቅስቀሳ የምረጡኝ ዘመቻ ሲያከናውኑ እንደነበር ገልፀዋል። በከተማው " ከገዢው ፓርቲ በመቀጠል ጠንካራ የቅስቀሳ ስራ ሰርቻለሁ" በማለት ስለ እንቅስቃሴያቸው አስረድተዋል።
"ከሞላ ጎደል" ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበር ለዶይቼ ቬለ የተናገሩት እጩ ተወዳዳሪው " ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ በፀጥታ አካላትም እንዲሁም ከነሱ ጋር በሚሰሩ ተባባሪ ካድሬዎች ከፍተኛ የስም ማጥፋት ፣ ሀሰተኛ መረጃዎችን የማሰራጨት በሀሰተኝነት የመወንጀል ዘመቻዎች እና ማስፈራሪያዎች ነበሩ" ብለዋል።
ዶክተር ሀብታሙ አጋጠሙኝ ያሏቸውን እነዚህን ነገሮች "ህግና ስርዓት ተከትዪ ለፀጥታ እና ፍትህ ተቋማት እንዲሁም ለምርጫ ቦርድ በማስረጃ አስደግፌ አመልክቻለሁ" በማለት አስረድተዋል።ላቀረብኩት አቤቱታ "ተገቢ ፣ ህጋዊና አጥጋቢ ምላሽ ባለማግኘቴ ምክንያት እና ህግ ለሁሉም እኩል አለመሆኑን በማየቴ ራሴን ከምርጫው ሂደት ለማግለል ተገድጃለሁ " ብለዋል።በሌላ በኩል በዚሁ ሀገራዊ ምርጫ በሀረሪ ለክልል ምክር ቤት በግል እጩነት የቀረቡት አቶ ጀማል አባገሮ ያለምንም እንከን የምረጡኝ ቅስቀሳ እያከናወኑ መሆኑን ለዶይቼ ቬለ ገልፀዋል። አቶ ጀማል በቀሪዎቹ ቀናት ቀሪ ያሏቸውን ስራዎች ለመስራት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ