1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሪያል ማድሪድ ወይንስ ባዬርን ሙይንሽን?

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 22 2016

በአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የደርሶ መልስ ግጥሚያ የመጀመሪያ ፍልሚያ ዛሬ ማታ ይከናወናል ። የጀርመኑ ባየርን ሙይንሽን ዛሬ በአሊያንትስ አሬና ስታዲየም የስፔኑ ሪያል ማድሪድን ያስተናግዳል ። ዛሬ ማታ ማን ያሸንፍ ይሆን ?

https://p.dw.com/p/4fLMC
Fußball Champions League | Bayern München - Real Madrid | Toni Kroos und Thomas Müller
ምስል Frank Hoermann/Sven Simon/IMAGO

በአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የደርሶ መልስ ግጥሚያ የመጀመሪያ ፍልሚያ ዛሬ ማታ ይከናወናል ። የጀርመኑ ባየርን ሙይንሽን ዛሬ በአሊያንትስ አሬና ስታዲየም የስፔኑ ሪያል ማድሪድን ያስተናግዳል ።

እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር ከ1976 ጀምሮ ሁለቱ ቡድኖች 12 ጊዜ ለግማሽ ፍጻሜ ተገናኝተዋል ። ሪያል ማድሪድ ሰባት ጊዜ አሸንፎ ወደ ፍጻሜ ሲያልፍ፤ ባዬርን ሙይንሽን አምስት ጊዜ ድል ቀንቶታል ።  ሪያል ማድሪድ ለ14 ጊዜያት የአውሮጳ ሻምፒዮንስ ዋንጫ በማንሳት ከአውሮጳ ቡድኖች ቀዳሚ መስመር ላይ ተሰልፏል ። በአንጻሩ ባዬርን ሙይንሽን የአውሮጳ ሻምፒዮንስ ዋንጫን ለ6 ጊዜያት አሸንፎ ወስዷል ።

ዛሬ ማታስ ማን ያሸንፍ ይሆን ?

በአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ የባዬርን ሙይንሽን እና ሪያል ማድሪድ ግጥሚያ
በአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ የባዬርን ሙይንሽን እና ሪያል ማድሪድ ግጥሚያ ። ከስድስት ዓመታት በፊት አንድ እኩል የወጡበት ጨዋታ ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል Andreas Gebert/dpa/picture alliance

ዛሬ ማታ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ባዬርን ሙይንሽን እና ሪያል ማድሪድ የመልስ ጨዋታቸውን የሚከናውኑት በሳምንቱ ረቡዕ ነው ። የፊታችን ረቡዕ ደግሞ፦ ሌለኞቹ የሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚዎች የጀርመኑ ቦሩስያ ዶርትሙንድ እና የፈረንሳዩ ፓሪ ሳንጃርሞ በሲግናል ኢዱና ፓርክ ይጋጠማሉ ። የአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግና የአውሮጳ ሊግ ፍልሚያዎች

የአውሮጳ ሊግ

በአውሮጳ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የደርሶ መልስ ግጥሚያ የመጀመሪያ ጨዋታዎች የፊታችን ሐሙስ ይከናወናሉ ። የፈረንሳዩ ማርሴ የጣሊያኑ አታላንታን ያስተናግዳል ። አታላንታ ለግማሽ ፍጻሜ ሲደርስ በታሪኩ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ። የመልስ ጨዋታዎች በሳምንቱ ይከናወኑና የዋንጫ ተፋላሚዎች ይለያሉ ። ሐሙስ ማታ በተመሳሳይ ሰአት የጣሊያኑ ሮማ የጀርመኑን ቡንደ ሲላ ዋንጫን የውድድር ዘመኑ ሳይጠናቀቅ መውሰዱን ካረጋገጠው ባዬርን ሌቨርኩሰን ጋ ይጋጠማል ። ባዬርን ሌቨርኩሰን ለግማሽ ፍጻሜ ሲደርስ ለአምስተኛ ጊዜ ነው ። በአንጻሩ ሮማ በአውሮጳ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ውድድር ሲበቃ ይህ አራተኛ  ሆኖ ተመዝግቦለታል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ