1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከፕሬዚዳንት ፑቲን ዳግም ምርጫ በኋላ በሩሲያ ለውጦች ይኖሩ ይሆን?

ማክሰኞ፣ መጋቢት 10 2016

በሩሲያ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በመጀመሪያ ደረጃ ውጤት መሠረት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ሩብ ክፍለ ዘመን የሚጠጋውን የስልጣን ዘመናቸውን ለተጨማሪ ስድስት ዓመታት ሊያራዝሙ ነው። እንደ ማዕከላዊ ምርጫ ኮሚሽን ከሆነ፣ ፑቲን 87 በመቶ የሚሆነውን ድምፅ አሸንፈዋል ።ለመሆኑ ፑቲን ከምርጫ በኋላ በሩሲያን ለውጦች ያደርጉ ይሆን?

https://p.dw.com/p/4duOv
የሩሲያ  ማዕከላዊ ምርጫ ኮሚሽን እንደገለፀው ፣ ፑቲን 87 በመቶ የሚሆነውን ድምፅ አሸንፈዋል
የሩሲያ ማዕከላዊ ምርጫ ኮሚሽን እንደገለፀው ፣ ፑቲን 87 በመቶ የሚሆነውን ድምፅ አሸንፈዋልምስል AFP/Getty Images/M. Antonov

ከፕሬዚዳንት ፑቲን ከዳግም ምርጫ በኋላ በሩሲያ ለውጦች ይኖሩ ይሆን?


በሩሲያ በቅርቡ የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሀገር ውስጥም ይሁን በዓለም ዙሪያ ለይምሰል የተካሄደ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው።ለዚህም ይመስላል በምርጫው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በድጋሚ ማሸነፋቸው ብዙዎችን አላስደነቀም።የፕሬዝዳንት ፑቲን አሸናፊነትና የምዕራባውያን አስተያየት
በሀምቡርግ ዩኒቨርሲቲ የሰላም ጥናትና ደህንነት ፖሊሲ ተመራማሪ የሆኑት ሬጂና ሄለር እንደገለፁት «ይፋ የሆነው 87 በመቶ የምርጫ ውጤት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን አምባገነናዊ የፑቲን አካሄድ እና አገዛዝ የሚያረጋግጥ ነው። ተመራማሪዋ አያይዘውም «ውጤቱ የመራጮችን ፍላጎት ሳይሆን የአገዛዙን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው» ይላሉ። የምርጫ ውጤቱም ቢሆን ለፑቲን ድርጊት ነፃ ፈቃድ ነው ይላሉ። «በመጨረሻ ይህ ለገዥው አካል ፣ለፑቲን ፖሊሲዎች እና ዩክሬን ውስጥ ለተከተለው ፖሊሲ እና ድርጊት ጭምር እንደ ነፃ ፈቃድ የሚያገለግል ነው።»ሲሉ ገልፀዋል።
የምስራቅ አውሮፓ ተንታኝ የሆኑት ሃንስ ሄኒንግ ሽሮደር በበኩላቸው የፑቲን አገዛዝ በ2023 ካጋጠመው ቀውስ ወዲህ የተረጋጋ ነበር ።እንደ ሽሮደር ክሬምሊን ባለፈው አመት የግል ሚሊሺያ ባላቸው የዋግነር ቡድን መሪ በሆኑት እና በአውሮፕላን አደጋ በሞቱት የፈገኒ ብሪጎዥን ችግር ተጋርጦበት የነበረ ቢሆንም፤ በኋላ ግን  ፑቲን  ስልጣናቸው መደላደሉን ገልፀዋል።
ባለሙያዎቹ እንደሚሉት የፑቲን አገዛዝ በስልጣን ላይ የቆየው፤ በተለያዩ ምክንያቶች ሲሆን ከነዚህም መካከል የሩስያ የተረጋጋ ኢኮኖሚ እና የምዕራባውያን ማዕቀብ በመቀነሱ ነው። በተጨማሪም ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጦርነት የሚቃወም  ሰውም ከፍተኛ አፈና ይደርስበታል። ይህ ሁሉ ተደማምሮ ክሪምሊን የቀድሞውን አገዛዝ እንዲቀጥል አስችሎታል ብለዋል። ከዚህ አንፃር ሬጂና ሄለር እንደሚሉት «አሁን የምናየው ነገር ቢኖር ፑቲን ምናልባትም  በተባባሰ ሁኔታ እና በከፍተኛ ጥንካሬ በዩክሬን ላይ ጦርነት እንደሚቀጥሉ ነው።»

የሩሲያ ባለስልጣናት ሩሲያ በያዘቻቸው የዩክሬን ግዛቶችም ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አካሂደዋል
የሩሲያ ባለስልጣናት ሩሲያ በያዘቻቸው የዩክሬን ግዛቶችም ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አካሂደዋልምስል Alexei Konovalov/TASS/dpa/picture alliance

የፑቲንን የጦርነት ፍላጎት ለመሙላት ከፍተኛ ቀረጥ?
በሌላ በኩል ፑቲን ከምርጫው በፊት በፌዴራል ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር የሩሲያ መንግስት  የግብር  ማሻሻያ ሀሳቦችን  እንዲያቀርብ በመጠየቃቸው ሩሲያውያን የግብር ጭማሪ ሊገጥማቸው እንደሚችል ተንታኞች ይገልፃሉ። ምክንያቱም ይላሉ ሽሮደር በዩክሬን ያለው ጦርነት ብዙ ገንዘብ የሚያስወጣ  ነው።«የሩስያ መንግስት አሁን እያደረገ ያለውን ጦርነት ጨምሮ ሁሉም ነገር ብዙ ገንዘብ ያስከፍላል። እና ይህ በከፊል በሚደረገው የግብር ጭማሪ ይካካሳል።» በኢንስብሩክ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ጌርሃርድ ማንጎት በበኩላቸው «መንግስት ገንዘብ ያስፈልገዋል፣ እና ይህ ሊገኝ የሚችለው የቀረጥ ገቢን በመጨመር ብቻ ነው ። ይህ ተጨማሪ የቀረጥ ገቢም  በዋናነት ለጦርነቱ ድጋፍ ይውላል»ብለዋል።የምርጫ ዝግጅት በሩሲያ

ተጨማሪ ወታደሮች ምልመላ?
ከግብር በተጨማሪ ከምርጫ በኋላ ብዙ ሩሲያውያን ወታደሮችን ለመመልመል አዲስ ቅስቀሳ ይጀመራል ብለውይጠብቃሉ።ፑቲን የሚያደርጉትን ወታደራዊ ንግግር እየቀነሱ ባለመሆናቸው ይህ እንደ ተጨባጭ ሁኔታ ይታያል ሲሉ ሄለር ለDW ተናግረዋል። የምዕራባውያን ድጋፍ ለዩክሬን አነስተኛ መሆንም ለፑቲን ሌላው ዕድል ነው ይላሉ።
«ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚሰጡት ድጋፍ የሚፈለገውን ያህል ጠንካራ እንዳልሆነ እናያለን።ይህም  በጦርነቱ ውስጥ ያለውን የኃይል ሚዛን ለመቀየር እና በአዲስ ቅስቀሳ እንደገና ለመሞከር ጥሩ መስኮት ነው።» ይሁን እንጂ፣ አሁን በሩሲያውያን ዘንድ በጦርነቱ ከፍተኛ መሰላቸት ስላለ፣ አዲስ የመመልመሉ እንቅስቃሴ አደገኛ ሊሆን ይችላል ሲሉ ሄለር ተናግረዋል። ማንጎትም ከፍ ያለ የቅስቀሳ ጥሪ አለመኖሩን የሚጠቁሙ የዳሰሳ ጥናቶችን በመጥቀስ በሀሳቡ ይስማማሉ ።ሽሮደር ግን አዲስ ቅስቀሳ ይኑር አይኑር ሩሲያ በሚቀጥሉት ወራት ለዩክሬን ባላት እቅድ ላይ የተመሰረተ ነው ይላሉ። «በወረራ ዩክሬንን ለማሸነፍ ከፈለጉ የታጠቀ ሀይላቸውን በማሳደግ ሀገሪቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ይጥራሉ።»በማለት ይገልፃሉ።ሆኖም ባለሙያው እንደሚሉት ሩሲያ ስኬታማ ለመምሰል እየሞከረች ሲሆን፤ በእሳቸው ግምት ቢያንስ እስከ አሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድረስ የበላይነቱን ማስቀጠል እና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ በድል ጎዳና ላይ መሆናቸውን ማሳየት ነው።በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዶናልድ ትራምፕ ከተሸነፉ የዩክሬን ሁኔታ የከፋ ይሆናል ይላሉ። እንደዚያ ከሆነ ሩሲያ በትልቅ የቅስቀሳ ዘመቻ ተጨማሪ ወታደሮችን መመልመል አያስፈልጋትም ሲሉ ሽሮደር ለDW ተናግረዋል።የዘንድሮው የሩሲያ ፓርላማ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ብላድሚር ፑቲን በዘንድሮው ምርጫ 87 በመቶ በማግኘት ማሸነፋቸው ተገልጿል
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ብላድሚር ፑቲን በዘንድሮው ምርጫ 87 በመቶ በማግኘት ማሸነፋቸው ተገልጿልምስል Maxim Shemetov/REUTERS

የአመራር ለውጥ?
በቅርቡ ከተካሄደው ምርጫ በኋላ በሩሲያ አመራር ትልቅ ለውጥ አይጠበቅም ሲሉ ባለሙያዎቹ ለDW ተናግረዋል። «በአሁኑ ጊዜ ምንም አይነት ዋና ድክመቶች አይታየኝም። ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚሹስቲን በግልጽ ጥሩ ስራ እየሰሩ ነው። በተጨማሪም የማዕከላዊ ባንክ እና የኢኮኖሚ ሚኒስትሩ የፑቲንን መንግስት ከዩክሬን ጥቃት በኋላ እንዳረጋጉ መነገር አለበት።» ሲሉ ሽሮደር ተናግረዋል።  በዩክሬን ጦርነት ምክንያት የአውሮፓ ህብረት እና የአሜሪካ ማዕቀብ ያልተጠበቀ ውዥንብር ካስከተለ በኋላ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ እና የፋይናንስ ፖሊሲ አውጪዎች ኢኮኖሚውን አረጋግተዋል። የዋጋ ንረቱም ቁጥጥር ስር ነው። ሩሲያ ከአውሮፓ ወደ እስያ ባደረገችው የኢኮኖሚ ሽግግር ጥሩ ውጤት ያስመዘገበች ሲሆን፤ከዚህ አንፃር ፑቲን ጣልቃ ለመግባት ምንም ምክንያት የላቸውም ብለዋል ሽሮደር።ፑቲን ለህዝቡ ባደረጉት ንግግር ሩሲያ ጦርነትን የሚደግፍ አዲስ ልሂቃን እንደሚያስፈልጋት አሳስበዋል። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹን ፑቲን  የታማኝ አጋሮቻቸውን ወንድ እና ሴት ልጆች ሊመለመሉ ይችላሉ። ሲል ሄለር ለDW ተናግረዋል። ከፑቲን በኋላ በእነዚህ ልሂቃን የተረጋጋ የስልጣን ሽግግርን ለማድረግ የረዥም ጊዜ ግብ በማዘጋጀት ተሃድሶ ሊደረግ ይችላል ብለው ያስባሉ።

ፀሀይ ጫኔ
ታምራት ዲንሳ