«መንታ መንገድ» ድራማ ክፍል 1 ገቢር ከ1-26 | በማ ድመጥ መማር | DW | 11.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

በማ ድመጥ መማር

«መንታ መንገድ» ድራማ ክፍል 1 ገቢር ከ1-26

ምሕረት፣ ዳንኤል እና ንጉሤ የመንታ መንገድ ተከታታይ ድራማ ባለታሪኮች ናቸው። ከባድ አማራጮችን ይጋፈጣሉ፤ ሕይወታቸውም እስከወዲያኛው ይቀይራል።

ምሕረት አሳክታዋለች! በሀገሪቱ ምርጥ ከሚባሉት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱ በሆነው ቦንጎ አካዳሚ የነጻ ትምህርት ዕድል አግኝታለች። በተጎሳቆለ መንደር ውስጥ ለምትኖረው የ15 ዓመቷ ታዳጊ ወጣት ይህ በሕይወቷ ሙሉ የምታልመው ነገር ዕውን መሆን ማለት ነው። እቤት ውስጥ ኑሮ ቀላል አይደለም። ታናናሽ መንታ ወንድሞቿ፤ እንክብካቤ አደርግላቸዋለሁ ብላ ቃል በመግባት የወሰደቻቸው አክስቷ ዘንድ ነው ያሉት። ነፍሰጡር እናቷ ሌላ ልጅ እየጠበቁ ነው። አክስቷ ግን ቃላቸውን ይጠብቁ ይሆን? የምሕረት አዲሷ ጓደኛ ትዕግስት የክፍል ጓደኛዋ በቦንጎ አካዳሚ ቆይታዋ ግር እንዳይላት እያለማመደቻት ነው፤ ሆኖም ተፅዕኖዋ ምን ያህል ቀና ይሆን? ሁለት ወንድ ተማሪዎች ከምህረት ፍቅር ሲይዛቸው ደግሞ ችግሮች መፈጠር ይጀምራሉ። የክፍል ጓደኞቿ ዳኒ እና ንጉሤ ምሕረትን በፍቅር ሊማርኳት ጥረት ያደርጋሉ፤ ግን ከሁለት አንዱ ችግር ላይ ሳይጥላት አይቀርም።

ክሪስፒን ምዋኪዴዮ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic

Downloads