1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕብር «ሕገ-ወጥ መንግሥት» ያለዉን ለመቀበል መቸገሩን ገለፀ

ሐሙስ፣ ሰኔ 11 2012

አሁን ያለዉን «ሕገ-ወጥ መንግሥት» ያለዉን መንግሥት ለመቀበል እንደሚቸገር ሕብር ኢትዮጵያ የተባለዉ ፓርቲ አሳወቀ። ፓርቲዉ ትናንት ባወጣዉ መግለጫ እንዳመለከተዉ የመንግሥት ስልጣን የማራዘመ ሂደት ባለድርሻ አካላትን ያላወያየ ሲል ወቅሶአል።  

https://p.dw.com/p/3dzlx
Äthiopien Addis Abeba | Logo | Hibir Ethiopia Democratic Party

ስልጣኑን በምክር ቤት በኩል በማራዘም እራሱን አዲስ አደገኛ አምባገንን እያደረገ ነዉ

አሁን ያለዉን «ሕገ-ወጥ መንግሥት» ያለዉን መንግሥት ለመቀበል እንደሚቸገር ሕብር ኢትዮጵያ የተባለዉ ፓርቲ አሳወቀ። ፓርቲዉ ትናንት ባወጣዉ መግለጫ እንዳመለከተዉ የመንግሥት ስልጣን የማራዘመ ሂደት ባለድርሻ አካላትን ያላወያየ ሲል ወቅሶአል። የብሔራዊ መግባባት እና የምክክር መድረክን በመግፋት በሕገ-ወጥ መንገድ የራስን ስልጣን ላራዘመ የፖለቲካ ፓርቲ የመንግሥትነት እዉቅናን ለመስጠት እንቸገራልን ይላል የሕብር ኢትዮጵያ መግለጫ ። ለእዉነተኛ ሽግግር ያልተዘጋጀዉ እና በባዶ የቃላት ሽንገላ እና በተራ ቡድንተኝነት ብቻ ለመጓዝ የሞከረዉ የለዉጥ ኃይል የፖለቲካ ስልጣኑን መቶ በመቶ ለመቆጣጠር የሞከረዉ በምክር ቤት በኩል በማራዘም እራሱን አዲስ አደገኛ አምባገንን ከማድረጉም በላይ ከዚህ ቀደም ያልታዩ እና ያልተሰሙ ኢሰብዓዊ ያላቸዉን ድርጊቶች ሲፈፅም ማየት ችለናል ብሎአል ።  ዝርዝሩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ልኮልናል። 

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ