ኅብረተ ሰብየመካከለኛው ምሥራቅ
ሒውማን ራይትስዎች በሳዑዲ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች
ዓርብ፣ ሐምሌ 23 2013ማስታወቂያ
በሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ተባብሶ የቀጠለው እንግልትና ስቃይ አሳስቦኛል ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች ገለፀ።
በድርጅቱ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብት ተመራማሪ ናድያ ሃርድማን በተለይ ለዶይቸ ቬለ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በደል በተመለከተ ድርጅታቸው ለሳዑዲ መንግስት ሪፖርት ቢያቀርብም እስካሁን ምላሽ አላገኘም። በኢትዮጵያኑ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የመብት ረገጣ ተከታትሎ የማጋለጡን ተግባር ድርጅታቸው አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተመራማሪዋ ጠቁመዋል።
ታሪኩ ኃይሉ
ሸዋዬ ለገሰ