ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ቻያ የተባለ ተክል ለማስተዋወቅ ምርምር ላይ ነው | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 23.01.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ቻያ የተባለ ተክል ለማስተዋወቅ ምርምር ላይ ነው

የሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ አይረን እና ቫይታሚን ኤ እጥረት ላለባቸው አካባቢዎች ይበጃል ባለው ቻያ የተባለ ጎመን መሰል ተክል ላይ ምርምር እያደረገ ነው። የዩኒቨርሲቲው ተማራማሪ ዶክተር ካሱ መሐመድ ተክሉ ድርቅ በመቋቋም ረገድ ብርቱ እንደሆነ ተናግረዋል። ቻያ የተባለውን ተክል ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት የጥበብ ባለሙያው አለፈለገ ሰላም ናቸው

አውዲዮውን ያዳምጡ። 07:38

የሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጎመን መሰሉ ቻያ ተክል ላይ ምርምር እያደረገ ነው

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ሁለት አመታት ለሀገር ፈይዳ ያላቸው አንድ መቶ አምሳ ስድስት የምርምር ፕሮጀክቶችን ስፖንሰር በማድረግ ሲያከሂድ ቆይቷል ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከነዚሁ ፕሮክቶች አንዱ የሆነውንና ለሁለት አመታት ያክል ጥናትና ምርምር ሲያካሂድበት የቆየውን "ቻያ" የተባለ ተክል ዝርያ ውጤት ከዳር በማድረስ ሰሞኑን ለባለሞያዎችና በዩኒቨርሲቲው ዙርያ ለሚገኙ የድሬደዋና ሀረሪ ክልል የጝብርና ሀላፊዎች ፣ ባለሞያዎችና አርሰሶ አደሮች ይፋ አድርጓል ፡፡

ተመራማሪዎች የዩኒቨርሲቲው የስራ ሀላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የጥናትና ምርምር ውጤቱ ይፋ የተደረገው ጎመን መሰል "የቻያ"ተክል ወደ ሀገር ውስጥ ከመጣ ከአምስት አስርት አመታት በላይ ዕድሜን ያስቆጠረና የሀገሪቱ ትልቅ የስነ ጥበብ ባለሞያ በሆኑ ግለሰብ የመጣ መሆኑን በተክሉ ላይ ምርምር እንዲካሄድ ለሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ያመጡት ወ/ሮ በቀለች በዚያው ግዜ ተናግረዋል ፡፡

በግብርናው ዘርፍ የላቀ የምርምር ውጤት በሚያከናውኑ ባለሞያዎች ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰርና የዚሁ የቻያ ተክል ጥናት ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ካሱ መሀመድ በዩኒቨርሲቲው ለጥናት ተመራጭ የሆነበትን ምክንያት በሚመለከት ተከታዩን ገልፀዋል ፡፡

እንደ ተመራማሪው ገለፃ ታዲያ ዝናብ አጠር በመሆናቸው ለድርቅና ሌሎች ችግሮች ተጋላጭ የሆኑትን የምስራቅ ሀገሪቱ አካባቢዎች ከግምት ያስገባው በ"ቻያ" ተክል ላይ የተደረገው ጥናትና ምርምር በሁለት ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል  ፡፡

በሀረማ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ተካሂዶበት ከዳር የደረሰውን የቻያ ተክል እንዴት ተክሎ ማራባት እንደሚቻል እና በተለይም ለምግብነት ለማዋል ዝግጁ ሆኖ መቆረጥ ስለሚችልበት አግባብ ዶ/ር ካሱ መሀመድ ተከታዩን ማብራርያ ሰተዋል ፡፡

በሀረማያ ኒቨርሲቲ ምርምር እና ጥናት ውጤት መሰረት የቻያ ተክል ለምግብነት አገልግሎት የሚውል ነው በዚህ ረገድም ምርምሩ ተደርጓል ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ጥናት ምክትል ፕሪዝዳንት ፕሮፌሰር ከበደ ወ/ፃዲቅ በበኩላቸው የቻያ ተክል የምግብ ዋስትና ችግር ላለባቸው የምስራቅ ሀገሪቱ አካባቢዎች ማግኘት መታደል መሆኑን ገልፀው ተክሉን በማስፋፋት ተገቢውን ውጤት ማምጣት እንዲችል ማድረግ ይገባል ብለዋል ፡፡

Äthiopien Haramaya University, Forschung Chaya-Pflanze | Kassu Mohammed, Forscher

ዶክተር ካሱ መሐመድ

የጥናትና ምርምር ውጤቱ ይፋ በተደረገበት ዝግጅት ላይ ከድሬደዋና ሀረር የተውጣጡ ባለሞያዎች አርሶ አደሮችና የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን ከሀርር የመጡት አቶ …የተክሉን ውጤታማነት በክልሉ ባሉ የገበሬ ማሰልጠኛ ተቋማት FTC ቀድሞ በመሞከር ለአርሶ አደሩ እንዲሰራጭ ይደረጋል ብለዋል ፡፡

አርሶ አደርች በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው አጥንቶ ወታውን የቻያ ተክል ወስደው እንደሚተቀሙበት ተናግረዋል ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ሁለት አመታት የቻ ተከልን ጨምሮ ከሁለት መቶ በላይ የጥናት ስራዎችን ማከናወኑና እና ለውጤት የበቁ ጥናቶችን ዩኒቨርሲቲው ባለው የገበሬ ማሰልጠኛ ተቋማት FTC በማራባት ለአርሶ አደሩ በስፋት የማሰራጨት ስራ እንደሚሰራ ተገልፃል፡፡

መሳይ ተክሉ

እሸቴ በቀለ

 

Audios and videos on the topic