ለቦይንግ 737 ሰለባ ቤተሰቦች ካሣ ጥያቄ
ዓርብ፣ ነሐሴ 3 2011ማስታወቂያ
በአሜሪካን ሕግ አንድን የመንግሥት አካል ከመክሰስ በፊት ያጠፋኸውን ጥፋት ጠቅሶ ሊከፈል የሚገባው የገንዘብ ካሣ መጠን ተጠቅሶ በማመልከቻ መጠየቅ እንደሚቻል ያመለከቱት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው አቶ ሸክስፒር ፈይሳ፤ በዚሁ መሠረት የካሣ ጥያቄውን ማቅረባቸውን ለዶይቼ ቬለ DW ገልጸዋል። ከአምስት ወራት በፊት እንደተነሳ ብዙም ሳይቆይ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በተከሰከሰው ቦይን አውሮፕላን የበረራ ሠራተኞችን ጨምሮ 157 ሰዎች ተሳፍረው ነበር። በጉዳዩ ላይ የሕግ ባለሙያውያን ያነጋገረው የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ