1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህወሓት እያካሄደ በሚገኘው ጉባኤ ላይ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ምን አሉ?

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 7 2016

14ናው የህወሓት ጉባዔ በርካታ የፓርቲው አባላት በተገኙበት ዛሬ ከሰዓት በኋላ መቀሌ ከተማ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጀምሯል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት በፓርቲ ውስጥ የተፈጠረው ክፍልል በንግግር እንዲፈታ ነው።

https://p.dw.com/p/4jQU9
Generalversammlung der TPLF wird von Nationaler Wahlbehörde Äthiopiens (NEBE) nicht anerkannt
ምስል Million Haileselassie/DW

14ኛው የሕወሓት ጉባዔ መጀመር እና የነዋሪዎች ስጋት

ሕዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ ሕወሓት 14ኛ መደበኛ ጉባኤዉን ማካሄድ ጀመረ ። በኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ዕቅቅና የተነፈገው ህወሓት የትግራይ ክልል የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 14 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ባልተገኙበት ነው። በርካታ  የፓርቲው አባላት በተገኙበት ጉባኤው ዛሬ ከሰዓት በኋላ መቀሌ ከተማ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጀምሯል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች  እንደሚሉት በፓርቲ ውስጥ የተፈጠረው ክፍልል በንግግር እንዲፈታ ነው። 

ሕወሓት በ50 ዓመት ታሪኩ አጋጥሞት በማያውቅ ፈተና ውስጥ እንዳለ ዐሳወቀ

በተጨማሪም  የህወሓት ጉባኤ ተከትሎ ከፌደራል መንግስት እየተሰነዘሩ ያሉ አስተያየት ስጋት የሚፈጥሩ ያሉዋቸው ሲሆን፥ ሌሎች ደግሞ አንድ ፓርቲ ጉባኤ አደረገ ተብሎ ወደ ግጭት የሚገባበት ሁኔታ ሊኖር እንደማይገባ፣ ህዝብ በጦርነት ማስፈራራት እንዲቆም የጠየቁም አሉ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ 

ኂሩት መለሰ